የጤና ሚኒስቴር የፀሐይ ኃይል መሳሪያዎችንና ሞተር ሳይክሎችን ለክልሎች አስረከበ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየጤና ሚኒስቴር የፀሐይ ኃይል መሳሪያዎችንና ሞተር ሳይክሎችን ለክልሎች አስረከበ
የጤና ሚኒስቴር የፀሐይ ኃይል መሳሪያዎችንና ሞተር ሳይክሎችን ለክልሎች አስረከበ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 06.03.2026
ሰብስክራይብ

የጤና ሚኒስቴር የፀሐይ ኃይል መሳሪያዎችንና ሞተር ሳይክሎችን ለክልሎች አስረከበ

ሚኒስቴሩ 380 የጤና ተቋማት የፀሐይ ኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎት እንዲያገኙ የሚያስችሉ የፀሐይ ኃይል ማመንጫ መሳሪያዎችን እና 1,183 በሀገር ውስጥ የተገጣጠሙ ሞተር ሳይክሎችን ለክልል የጤና ቢሮዎች አስረክቧል።

መሳሪያዎቹ የጤና ተቋማት አስተማማኝ የኤሌክትሪክ ኃይል እንዲያገኙ የሚያስችሉና አስቸጋሪ በሆኑ አካባቢዎች ክትባትና መድኃኒት ለማድረስ የሚረዱ መሆናቸውን የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር መቅደስ ዳባ በርክክቡ ላይ ተናግረዋል፡፡

"መንግሥት ለአየር ንብረት ተፅዕኖ የማይበገር የጤና ተቋማትን ለመገንባት እየሠራ ነው" ብለዋል።

ድጋፉ በተለይም በገጠር አካባቢዎች የሚታየውን የጤና አገልግሎት ፍትሐዊነት ክፍተት በመሙላት የእናቶች እና የሕፃናትን ጤና ለማሻሻል ትልቅ ፋይዳ ይኖረዋል ተብሏል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
የጤና ሚኒስቴር የፀሐይ ኃይል መሳሪያዎችንና ሞተር ሳይክሎችን ለክልሎች አስረከበ - Sputnik አፍሪካ
1/2
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
የጤና ሚኒስቴር የፀሐይ ኃይል መሳሪያዎችንና ሞተር ሳይክሎችን ለክልሎች አስረከበ - Sputnik አፍሪካ
2/2
1/2
2/2
አዳዲስ ዜናዎች
0