ጅማ ዩኒቨርሲቲ እና ቦይንግ ጅማን የአፍሪካ የኤሮስፔስ ትምህርት የልህቀት ማዕከል ለማድረግ የሚያስችል አጋርነት መሠረቱ
18:52 05.03.2026 (የተሻሻለ: 18:54 05.03.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ጅማ ዩኒቨርሲቲ እና ቦይንግ ጅማን የአፍሪካ የኤሮስፔስ ትምህርት የልህቀት ማዕከል ለማድረግ የሚያስችል አጋርነት መሠረቱ
ዩኒቨርሲቲው ከግዙፉ የአውሮፕላን አምራች ኩባንያ ጋር የተፈራረመው ስምምነት በጅማ ዩኒቨርሲቲ በቅርቡ የተቋቋመውን የኢቪዬሽን ሳይንስ እና ኤሮስፔስ ኢንጂነሪንግ አካዳሚ በሰው ኃይልና በቴክኖሎጂ ለማጠናከር ያለመ ነው ተብሏል።
በመጀመሪያው ምዕራፍ የመማሪያ ክፍሎችን ማዘመን፣ የመምህራን ሥልጠና እና የተማሪዎችን የፈጠራ ሥራዎች የሚያበረታታ "የኤሮስፔስ ኢንኖቬሽን ቻሌንጅ" ማካሄድን እንደሚያካትት ዩኒቨርሲቲው አስታውቋል።
ቦይንግ በበኩሉ፤ አፍሪካ በሚቀጥሉት 20 ዓመታት ፓይለቶችና ቴክኒሻኖችን ጨምሮ ከ74,000 በላይ አዳዲስ የኢቪዬሽን ባለሙያዎች እንደሚያስፈልጋት በመግለጽ፤ ይህ አጋርነት የአኅጉሪቱን የሰው ኃይል ፍላጎት ይቀርፋል ብሏል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X