ደቡብ አፍሪካ ለአዲስ የኤችአይቪ መከላከያ መድኃኒት የሀገር ውስጥ አምራች እየፈለገች መሆኑ ተዘገበ
17:46 05.03.2026 (የተሻሻለ: 17:54 05.03.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ደቡብ አፍሪካ ለአዲስ የኤችአይቪ መከላከያ መድኃኒት የሀገር ውስጥ አምራች እየፈለገች መሆኑ ተዘገበ
የደቡብ አፍሪካ መንግሥት የጊሊያድ ሳይንሰስ ኩባንያ ምርት የሆነውን እና በዓመት ሁለት ጊዜ ብቻ የሚወሰደውን 'ሌናካፓቪር' የኤችአይቪ መከላከያ መድኃኒት በሀገር ውስጥ ሊያመርት የሚችል ድርጅት የመለየት ሥራ መጀመሩን የብሪታንያ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።
መንግሥት ከዩኒታይድ እና ከአሜሪካ ፋርማኮፒያ ጋር በመተባበር የሀገር ውስጥ ኩባንያዎችን በመገምገም፤ በሕንድ፣ ግብፅ እና ፓኪስታን ከተሰጡት ስድስት የፈቃድ ስምምነቶች በተጨማሪ ሰባተኛው የፈቃድ ስምምነት ለማን ይሰጥ የሚለውን ሐሳብ ለጊሊያድ ኩባንያ እንደሚያቀርብ ተገልጿል።
የጉዳዩ አስፈላጊነት፦ ደቡብ አፍሪካ በዓለም ከፍተኛ በኤችአይቪ የተያዙ ( 8 ሚሊዮን) ሰዎች ይኖሩባታል። መድኃኒቱን በሀገር ውስጥ ማምረት በበሽታው መያዝን በእጅጉ እንደሚቀንስና በአጠቃላይ ቀጣናውን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ታምኖበታል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X