ኢትዮ ቴሌኮምን ጨምሮ ግዙፍ የአፍሪካ የቴሌኮም ተቋማት አዲስ የ40 ዶላር ስማርት ስልክ ለገበያ ሊያቀርቡ ነው
16:53 05.03.2026 (የተሻሻለ: 16:54 05.03.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢትዮ ቴሌኮምን ጨምሮ ግዙፍ የአፍሪካ የቴሌኮም ተቋማት አዲስ የ40 ዶላር ስማርት ስልክ ለገበያ ሊያቀርቡ ነው
ከ800 ሚሊዮን በላይ ደንበኞች ያሏቸው ግንባር ቀደሞቹ የአፍሪካ የቴሌኮም ተቋማት ኢትዮ ቴሌኮም፣ አክሲያን ቴሌኮም፣ ኤርቴል፣ ኤምቲኤን፣ ኦሬንጅ እና ቮዳኮም፤ የአኅጉሪቱን የዲጂታል አገልግሎት ተደራሽነት ለማስፋት በወቅታዊ ምንዛሬ 6 ሺህ ብር የሚያወጣ የ4G ስማርት ስልክ ለገበያ ለማቅረብ ማቀዳቸውን አስታውቀዋል።
ኢትዮጵያ፣ ናይጄሪያ፣ ኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ፣ ሩዋንዳ፣ ታንዛኒያ እና ኡጋንዳ ደግሞ ስልኩ መጀመሪያ ለገበያ የሚቀርብባቸው ሀገራት እንዲሆኑ ተመርጠዋል።
በአሁኑ ወቅት ከዓለም አቀፉ የሞባይል ኦፕሬተሮች ማኅበር ጋር በመተባበር በስልኩ ዝርዝር ይዘት ላይ ዝግጅት እየተደረገ እንደሚገኝ ተዘግቧል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X