እስራኤልና አሜሪካ ከኢራን ጋር የሚያደርጉት ግጭት ለዓለም አቀፍ አለመረጋጋትና ኢኮኖሚ ስጋት ነው - ላቭሮቭ

እስራኤልና አሜሪካ ከኢራን ጋር የሚያደርጉት ግጭት ለዓለም አቀፍ አለመረጋጋትና ኢኮኖሚ ስጋት ነው - ላቭሮቭ
"አሁን በጋዜጦች የፊት ገጽ፣ በቴሌቪዥን መስኮቶችና በማኅበራዊ ትስስር ገጾች ላይ የማይጠፋውና ለመላው ዓለም፣ ለሁሉን አቀፍ መረጋጋትና ለዓለም ኢኮኖሚ እጅግ ከፍተኛና አሉታዊ መዘዝ ያለውን ይህንን ቀውስ ሳልጠቅስ አላለፍም" ሲሉ የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ተናግረዋል።
ሌሎች ቁልፍ የላቭሮቭ መግለጫዎች፡-
◻ በአሜሪካ ውስጥ እንኳን በኢራን ዘመቻ እውነተኛ ግቦች ዙሪያ አለመግባባቶች አሉ።
◻ የእስራኤልና የአሜሪካ ጥቃት አንዱ ምክንያት በኢራን እና በባሕረ ሰላጤው ሀገራት መካከል መከፋፈልን መፍጠር ነው።
◻ የባሕረ ሰላጤው ሀገራት የኢራንን ጥቃቶች ሲያወግዙ የአሜሪካና የእስራኤልን ጥቃቶች ግን ችላ ይላሉ።
◻ የኢራን የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብት መከበር አለበት።
◻ ሩሲያ የባሕረ ሰላጤው ሀገራት አሜሪካና እስራኤል በኢራን ላይ የሚሰነዝሩትን ጥቃት ለማስቆም የሚደረገውን ጥረት እንዲቀላቀሉ ጥሪ ታቀርባለች።
◻ ሞስኮ በመካከለኛው ምስራቅ ያለውን ሁኔታ ለመፍታት የበኩሏን ጥረት ሁሉ ታደርጋለች።
◻ ኔቶ አሜሪካና እስራኤል በኢራን ላይ በጀመሩት ጦርነት ውስጥ ተሳታፊ እየሆነ ነው።
◻ በዋሽንግተን እና በቴህራን መካከል የነበረው ድርድር ለስኬት ተቃርቦ ነበር።
◻ ሚኒስትሩ በመካከለኛው ምስራቅ ለሲቪል ሰዎች ሞት ምክንያት በሚሆኑ ጥቃቶች ላይ እገዳ እንዲደረግ ሐሳብ አቅርበዋል።
◻ በተጨማሪም በመካከለኛው ምስራቅ ያለውን ግጭት በአስቸኳይ ለማስቆም የሚጠይቅ የውሳኔ ሐሳብ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት እንዲጸድቅ ሐሳብ አቅርበዋል።
◻ የኔቶ መሪ ሩተ አሜሪካ ኢራን ላይ ለከፈተችው ዘመቻ የጋራ መከላከያ ስምምነት አንቀጽን ማቅረባቸው የጥምረቱ ፍላጎት በሌላ አካል እንደሚመራ ያሳያል።
◻ ሩሲያ አሁን ላይ በዩክሬን ጉዳይ ከአሜሪካ ጋር የሚደረገው ድርድር ለሌላ ነገር መሸፈኛ ነው ብላ ለመጠራጠር ምንም ምክንያት አታይም።
◻ ሩሲያ በአንኮሬጅ ከአሜሪካ ጋር የተደረሱ ስምምነቶችን በዩክሬን ዕርቅ ለሚደረጉ ድርድሮች እንደ መነሻ ትመለከታቸዋለች።
◻ 'አርክቲክ ሜታጋዝ' በተባለው የሩሲያ ጋዝ ጫኝ መርከብ ላይ በተፈጸመው ጥቃት የዩክሬንን እጅ ለመደበቅ የተደረገ ሙከራ የለም።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X