ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ግዜ የዓለም አትሌቲክስ ውድድርን ለማስተናገድ ተመረጠች

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ግዜ የዓለም አትሌቲክስ ውድድርን ለማስተናገድ ተመረጠች
ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ግዜ የዓለም አትሌቲክስ ውድድርን ለማስተናገድ ተመረጠች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 05.03.2026
ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ግዜ የዓለም አትሌቲክስ ውድድርን ለማስተናገድ ተመረጠች

የዓለም አትሌቲክስ አኅጉራዊ ጉብኝት አካል የሆነው የአንድ ቀን ውድድር በመጪው ሚያዝያ 10 2018፤ በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ ዓለም አቀፉ ተቋም በመርኃ-ግብር ግዜ ማሳወቂያ ሰሌዳው ይፋ አድርጓል፡፡

‍‍ በውደድሩ ከተለያዩ ሀገራት የተወጣጡ እውቅ አትሌቶች ይሳተፋሉ ተብሏል፡፡

ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ውድድሩን ለማስተናገድ መመረጧ አዲስ ምዕራፍ ነው ሲል የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።

ይህ ዜና የዓለም አትሌቲክስ የውድድር ዋና ዳይሬክተር ፒርስ ኦክላጋን በየካቲት ወር መጀመሪያ በኢትዮጵያ የሁለት ቀን የሥራ ጉብኝት ማድረጋቸውን ተከትሎ የመጣ ነው፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0