አሜሪካና እስራኤል በኢራን ባካሄዱት ጥቃት የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ6 ሺህ በላይ ደረሰ
11:37 05.03.2026 (የተሻሻለ: 11:44 05.03.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
አሜሪካና እስራኤል በኢራን ባካሄዱት ጥቃት የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ6 ሺህ በላይ ደረሰ
2,500 የሚሆኑት ደግሞ ሆስፒታል መግባታቸውን የአደጋ ጊዜ አገልግሎቶች ገልፀዋል፡፡
ያለፉት 24 ሰዓታት አንኳር ክስተቶች፡-
◻ ኢራን ትናንት ምሽት በእስራኤል ላይ አዲስ የሚሳኤል ጥቃት ሰንዝራለች።
◻ በሆርሙዝ ሰርጥ የነዳጅ ጫኝ መርከቦች እንቅስቃሴ በመካከለኛው ምስራቅ እየተባባሰ በመጣው ግጭት ምክንያት በ90 በመቶ መቀነሱን ክፕለር የተባለው የጥናት ተቋም አስታውቋል።
◻ የኢራቅ ኩርዶች በኢራን ላይ ጥቃት ሰንዝረዋል የሚባለውን ዘገባ አስተባብለዋል።
◻ የኢራን ጦር ኃይሎች ጠቅላይ መምሪያ ወደ ቱርክ የሚሳኤል ጥቃት ተሰንዝሯል የሚሉ ዘገባዎችን ውድቅ አድርጓል።
◻ በግጭቱ ወቅት ቢያንስ 105 በኢራን የሚገኙ የሲቪል መሠረተ ልማቶች በእስራኤል እና በአሜሪካ ጥቃት ኢላማ መደረጋቸውን የቀይ ጨረቃ ድርጅት ገልጿል።
◻ የኢራን ኃይሎች በእስራኤል ራማት ዴቪድ የአየር ኃይል ጣቢያ የሚገኘውን የነዳጅ ማጠራቀሚያ መምታታቸውን የአካባቢው መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።
ስፑትኒክ በተለየ ያገኘው ተንቀሳቃሽ ምሥል የኢራን የመረጃ ሚኒስቴር ሕንፃ የጥቃት ኢላማ ሲሆን ያሳያል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X