የዓድዋ ድል 130ኛ ዓመት፦ የሩሲያ እና ኢትዮጵያ የፀረ–ቅኝ ግዛት አጋርነት ከዓድዋ ጦርነት ዋዜማ እስከ ዛሬ
20:27 04.03.2026 (የተሻሻለ: 20:34 04.03.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የዓድዋ ድል 130ኛ ዓመት፦ የሩሲያ እና ኢትዮጵያ የፀረ–ቅኝ ግዛት አጋርነት ከዓድዋ ጦርነት ዋዜማ እስከ ዛሬ
የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማሪያ ዛካሮቫ 130ኛውን የዓድዋ ድል በዓል አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት፣ ጦርነቱ በዓለም ታሪክ ውስጥ አንድ ትልቅ ክስተት ተደርጎ መወሰዱ ተገቢ ነው።
“የቅኝ ገዥ ኃይል በኢትዮጵያ ጦር መሸነፉ የሚያረጋግጠው የኢትዮጵያን ሕዝብ ጥንካሬ ብቻ ሳይሆን፤ የአፍሪካ ከቅኝ ግዛት ነፃ የመውጣት ጅማሮም ነው።” ብለዋል፡፡
ዛካሮቫ በጦርነት ላይ በኢትዮጵያ በኩል በኩባን ኮሳክስ ካፒቴን ኒኮላይ ሊዮንቲየቭ የሚመሩ ሩሲያውያን በፈቃደኝነት መሳተፋቸው አስታውሰዋል፡፡ ሩሲያውያን ለዓድዋ ድሉ ዝግጅት የነበራቸው ሚና ከተሳትፎ የላቀ እንደነበርም አስረድተዋል።
“ [...] ሩሲያ 30 ሺህ ጠመንጃዎችን፣ 5 ሚሊዮን ጥይቶችን እና 40 መድፎችን በፍጥነት እና በነፃ ለኢትዮጵያውያን ሰጥታለች። በተጨማሪም ሩሲያዊያኑ የጦርነቱን ስትራቴጂካዊ ዕቅድ በማዘጋጀት ረገድ ተሳትፋለች።” ሲሉ ታሪካዊ አስረጅ ጠቅሰው አብራርተዋል፡፡
ሩሲያ በዓድዋ ጦርነት ወቅት ለኢትዮጵያ ያደረገችውን እገዛ እና የአፍሪካ አገራት ከቅኝ ግዛት ቀንበር እንዲላቀቁ በማድረግ የነበራት ሚና ለማወቅ ቪዲዮውን ይመልከቱ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X