የኢራን፣ የአሜሪካ እና የእስራኤል ግጭት - የቅርብ ጊዜ መረጃዎች
19:51 04.03.2026 (የተሻሻለ: 19:54 04.03.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የኢራን፣ የአሜሪካ እና የእስራኤል ግጭት - የቅርብ ጊዜ መረጃዎች
እስራኤል በቴህራን ላይ አስረኛውን ዙር ጥቃት መፈፀሟን የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት የፕሬስ አገልግሎት ገልጿል፡፡
በአሜሪካ እና በእስራኤል ጥቃት የተገደሉ ሰዎች ቁጥር 1,045 መድረሱን፣ ታስኒም የዜና ወኪል የሰማዕታት እና የቀድሞ ታጋዮች ጉዳይ ፋውንዴሽንን ጠቅሶ ዘግቧል።
በደቡብ ምስራቅ ቴህራን የሚገኝ የመኖሪያ መንደር የቦምብ ጥቃት እንደደረሰበት ኢርና ዘግቧል።
በአሜሪካ እና በእስራኤል ጥቃቶች ምክንያት ቢያንስ ሦስት የህክምና ባለሙያዎች መገደላቸውን የኢራን ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።
የቱርክ መከላከያ ሚኒስቴር ከኢራን ግዛት ተነስቶ ወደ ቱርክ የአየር ክልል የተተኮሰ ባለስቲክ ሚሳኤል ማክሸፉን ገልጿል።
ተጨማሪ የአሜሪካ ኃይሎች ወደ መካከለኛው ምስራቅ እየገቡ ሲሆን፤ በኢራን ላይ የሚካሄደው ዘመቻ አስፈላጊውን ጊዜ ያህል እንደሚወስድ የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስትር ተናግረዋል።
በቪዲዮው ላይ፦ የአሜሪካ ቶርፒዶዎች (የውሃ ውስጥ ሚሳኤሎች)በስሪላንካ የባሕር ዳርቻ አቅራቢያ የኢራንን የባሕር ኃይል የጦር መርከብ ሲመቱ ይታያል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X