በትግራይ ጦርነት ወቅት የተፈጸሙ የሰብአዊ የመብት ጥሰቶች በሽግግር ፍትሕ መፈታት አለባቸው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

ሰብስክራይብ

በትግራይ ጦርነት ወቅት የተፈጸሙ የሰብአዊ የመብት ጥሰቶች በሽግግር ፍትሕ መፈታት አለባቸው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

የፌዴራል መንግሥት በግጭቱ ወቅት ለተፈጸሙ ጥቃቶችና ግፎች ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ ቁርጠኛ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ከመንግሥት ሚዲያ ጋር ባደረጉትና በማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ላይ ባጋሩት ቃለ መጠይቅ ላይ ገልፀዋል።

በፕሪቶሪያው ስምምነት መሠረት በሁሉም ተዋናይ ኃይሎች ተፈፀሙ የሚባሉ ጥሰቶች በሽግግር ፍትሕ እንዲታዩ መስማማታቸውን አስታውሰዋል፡፡

ዐቢይ አሕመድ፣ " ልጽ ለማድረግ፣ ይህ ምርመራና ተጠያቂነት በጦርነቱ ወቅት የተፈፀሙ ወንጀሎችን የሚመለከት ነው፡፡ ምክንያቱም [...] ጦርነቱን ያን ጊዜ ሕወሓት እንደጀመረው ሁሉም የሚያውቀው እና ፀሐይ የሞቀው ሀቅ ነው፡፡ ስለሆነም በበኩላችን የሕግ ጥሰት ገለልተኛ በሆነ መንገድ ማለትም በሽግግር ፍትሕ ሊጣራ ይገባል ብለን እናማናለን፡፡" ብለዋል፡፡

ፍትሕ ከፖለቲካዊ ውግንና ነጻ ሆኖ መረጋገጥ አለበት ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ይሁን እንጂ ይህ እንዳይሆን እያደናቀፈ ያለው “ያ ቆሞ ቀር ኃይል” (ሕወሓት) መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0