የመካከለኛው ምስራቅ ግጭት፦ አፍሪካ ቀዳሚዋ ተጎጂ ትሆናለች - ሴኔጋላዊ የምጣኔ ሀብት ባለሙያ

ሰብስክራይብ

የመካከለኛው ምስራቅ ግጭት፦ አፍሪካ ቀዳሚዋ ተጎጂ ትሆናለች - ሴኔጋላዊ የምጣኔ ሀብት ባለሙያ

​ ግጭቱ በመልካምድራዊ አቀማመጥ ከአፍሪካ ርቆ ቢገኝም፣ አኅጉሪቱ እጅግ የከፋ የኢኮኖሚ መዘዝ ሊደርስባት እንደሚችል የምጣኔ ሀብት ፕሮፌሰር አቡ ካኔ ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልጸዋል።

​“አፍሪካ ለሁሉም ዋና ዋና ላኪ አገራት ዋነኛ ገበያ በመሆኗ፣ ዓለም አቀፋዊ ቀውስ በሚከሰትበት ጊዜ ከማንኛውም አኅጉር በፊት ጉዳቱ የሚደርሰው በአፍሪካ ላይ ነው” ሲሉ አስረድተዋል።

​እንደ ፕሮፌሰር ካኔ ገለጻ፣ ሁኔታው በአፍሪካ ገበያዎች ላይ የዋጋ ንረትን የሚያስከትል ሲሆን፣ “የተወሰኑ የአቅርቦት ሰንሰለቶች መቋረጥን” ያመጣል።

በአፍሪካ አገራት መካከል የትብብር አስፈላጊነት

​ ባለሙያው የአፍሪካ አኅጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣናን በቁም ነገር መመልከት አስፈላጊ መሆኑን አሳስበዋል። ይህ ቀጣና በአፍሪካ አገራት መካከል ያለውን የንግድ ልውውጥ ሊያሳድግ እና በኢኮኖሚዎች መካከል ያለውን እርስ በርስ መደጋገፍ ሊያረጋግጥ እንደሚችል ገልጸዋል

​“በኢንዱስትሪ ልማት ላይ ኢንቨስት ማድረግ ይህንን ችግር ሊፈታው ይችላል፤ እንዲሁም አቅሙ ስላለ የአፍሪካ አገራት እርስ በርስ በስፋት እንዲገበያዩ ያስችላቸዋል” ሲሉ ባለሙያው ንግግራቸውን አጠቃለዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0