ሩሲያ ለግጭቱ ዲፕሎማሲያዊ መፍትሄ ለመፈለግ እገዛ ለማድረግ ዝግጁ መሆኗን ላቭሮቭ ለኢራኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አራግቺ ገለጹ
20:09 03.03.2026 (የተሻሻለ: 20:14 03.03.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ሩሲያ ለግጭቱ ዲፕሎማሲያዊ መፍትሄ ለመፈለግ እገዛ ለማድረግ ዝግጁ መሆኗን ላቭሮቭ ለኢራኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አራግቺ ገለጹ
የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የስልክ ውይይታቸውን በተመለከተ የሰጣቸው ተጨማሪ መግለጫዎች፡-
ላቭሮቭ እና አራግቺ የአሜሪካ እና የእስራኤል ድርጊቶች፣ መሠረታዊ ዓለም አቀፍ የሕግ ድንጋጌዎችን እየጣሱ መሆናቸውን እንዲሁም ለከፋ መዘዝ እንደሚዳርግ አጽንኦት ሰጥተው ተወያይተዋል።
ሁለቱ ሚኒስትሮች ትንኮሳ በላመጣው የአሜሪካ እና የእስራኤል ወታደራዊ ጥቃት ሳቢያ በቀጣናው ስላጋጠሙ ወቅታዊ ሁነቶች መክረዋል።
በመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት የሚገኙ ሲቪሎችን እና የሲቪል መሠረተ ልማቶችን ደህንነት ለመጠበቅ ቅድሚያ የሚሰጣቸው እርምጃዎች እንዲወሰዱ ሚኒስትሮቹ መክረዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X