የአሜሪካ፣ እስራኤል እና ኢራን ግጭት መባባስ ለናይጄሪያ የነዳጅ ዋጋ መዋዥቅና የደኅንነት ሥጋት ደቅኗል ተባለ

ሰብስክራይብ

የአሜሪካ፣ እስራኤል እና ኢራን ግጭት መባባስ ለናይጄሪያ የነዳጅ ዋጋ መዋዥቅና የደኅንነት ሥጋት ደቅኗል ተባለ

​ እየተካሄደ ያለው ግጭት በነዳጅ ዋጋ አለመረጋጋት፣ በጂኦፖለቲካዊ ጫናዎች እና በደኅንነት ተግዳሮቶች አማካኝነት በናይጄሪያ ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ ሊያሳድር እንደሚችል የናይጄሪያ የስጋት አስተዳዳሪዎች ማኅበር በመግለጫው አስጠንቅቋል።

የማኅበሩ ፕሬዝዳንት ዶክተር አባስ ኢድሪስ ካሰፈሩት መግለጫ የተወሰዱ ዋና ዋና ነጥቦች፦

የነዳጅ ገቢ፦ ናይጄሪያ ለዓለም አቀፍ የዋጋ ለውጦች በጣም ተጋላጭ ናት። ግጭቱ የአቅርቦት ሥጋትን በመፍጠር ዋጋን ሊጨምርና ገቢን ሊያሳድግ ይችላል፤ በሌላ በኩል ደግሞ የፍላጎት መቀነስን የሚያስከትል የኢኮኖሚ ድቀት በማስከተል ኢኮኖሚውን ሊጎዳው ይችላል።

የደኅንነት ሥጋቶች፦ "በመካከለኛው ምስራቅ ያለው አለመረጋጋት መጨመር ትኩረት ወደ ደኅንነት ወጪዎች እንዲዞር ሊያደርግ ይችላል፤ ይህም ለኢኮኖሚ ልማት የሚውሉ ሀብቶችን ይነጥቃል።" በተጨማሪም የመሣሪያዎች መሰራጨት እና ሊኖር የሚችል የስደተኞች ፍሰት ስጋት መሆናቸው ተገልጿል።

ኢኮኖሚያዊ ውድቀት፦ ሊከሰቱ የሚችሉ ተፅዕኖዎች፦ የንግድ መስተጓጎል፣ የገቢ ዕቃዎች ዋጋ መጨመር፣ የዋጋ ግሽበት፣ ከውጭ የሚላክ የገንዘብ መጠን መቀነስ እና የውጭ ኢንቨስትመንት መሳሳት ናቸው።

​ዶክተር ኢድሪስ መንግሥት ንቁ የሆነ የስጋት አስተዳደር ስልትን እንዲከተል አሳስበዋል። "የአንድ በርሜል ድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ እስከ 150 ዶላር ሊደርስ ይችላል" ሲሉም አስጠንቅቀዋል።

ቪዲዮው፣ በሳዑዲ አረቢያው የነዳጅ ኩባንያ አራምኮ ላይ በቅርቡ ተፈጸመ የተባለውን የድሮን ጥቃት ያሳያል፡፡

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0