የአሜሪካ "የሽብር ላይ ጦርነት" የኢራንን የ"ሞዛይክ" መከላከያ ስትራቴጂ እንዴት ቀረጸው

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየአሜሪካ "የሽብር ላይ ጦርነት" የኢራንን የ"ሞዛይክ" መከላከያ ስትራቴጂ እንዴት ቀረጸው
የአሜሪካ የሽብር ላይ ጦርነት የኢራንን የሞዛይክ መከላከያ ስትራቴጂ እንዴት ቀረጸው - Sputnik አፍሪካ, 1920, 03.03.2026
ሰብስክራይብ

የአሜሪካ "የሽብር ላይ ጦርነት" የኢራንን የ"ሞዛይክ" መከላከያ ስትራቴጂ እንዴት ቀረጸው

​ "ሞዛይክ መከላከያ ለረጅም ጊዜ የቆየ የኢራን ስትራቴጂ ሲሆን፣ እ.ኤ.አ በ2000ዎቹ አሜሪካ አፍጋኒስታን እና ኢራቅን በወረረችበት ወቅት እንዲሁም በኢራን የኒውክሌር መርሃ ግብር ዙሪያ የመጀመሪያው ቀውስ በተከሰተበት ወቅት የፀደቀ ነው" ይላሉ አንጋፋው ሩሲያዊ የወታደራዊ ጉዳዮች ታዛቢ ዩሪ ልያሚን።

በሞስኮ በሚገኘው የስትራቴጂዎች እና ቴክኖሎጂዎች ትንተና ማዕከል ከፍተኛ ተመራማሪ የሆኑት ልያሚን ሲያስረዱ፦ «አሜሪካ በአየር ኃይል፣ በደህንነት መረጃ (intelligence) እና በሌሎች ዘርፎች ያላትን የበላይነት ግምት ውስጥ በማስገባት፣ አብዛኛው ወይም ሁሉም የኢራን ከፍተኛ የጦር አዛዦች የመገደል አደጋ እንዳለባቸው ኢራን ተረድታ ነበር» ብለዋል።

​ሞዛይክ መከላከያ መሠረቱ «ለግዛታዊ ዕዞች፣ ለጦር ሰፈሮች እና ለሌሎች እርከኖች ከፍተኛ ሥልጣን መስጠት እንዲሁም ራሳቸውን ችለው የውጊያ ሥራዎችን እንዲያከናውኑ ማስቻል» ነው።

​ መካከለኛው ምስራቅ፣ አሁን ያለው ውጥረት ሞዛይክ መከላከያ በተግባር ሲፈተሽ የመጀመሪያው ነው፤ ምክንያቱም ስልቱ «በተለይ ከአሜሪካ ጋር ለሚደረግ መጠነ ሰፊ ጦርነት። ተብሎ የተነደፈ ነው» ሲሉ ልያሚን ጠቁመዋል።

የስትራቴጂው ዋነኛ ጥቅሙ የኢራንን ጠባቂዎች፣ "ወደ ተናጠል ሞዛይክ ቁርጥራጮች (የተበታተነ አደረጃጀት) መቀየር ሲሆን፣ ይህም ጥቂት 'ቁርጥራጮች' ቢጠፉም አጠቃላይ መዋቅሩ እንዳይፈርስ ያደርጋል። ይህም ከፍተኛ አመራሮችን ኢላማ ያደረጉ ጥቃቶች የሚያደርሱትን ተጽዕኖ በከፍተኛ ሁኔታ ይቀንሳል፤ ምክንያቱም በመሬት ላይ ያሉ ወታደሮች አስቀድሞ በተቀመጠው ዕቅድ ወይም የትዕዛዝ ሰንሰለቱ ካልተቋረጠ ከሚደርሳቸው አጠቃላይ መመሪያ በመነሳት ተግባራቸውን መቀጠል ይችላሉ።"

እንደ ልያሚን ገለጻ፣ ሞዛይክ መከላከያ "ስጋቶች" አሉት፡፡ ከእነዚህም መካከል ከጎረቤት የባሕረ ሰላጤው አገራት ጋር የሚደረጉ የተኩስ አቁም ስምምነቶች ላይ "መዘግየትን" መፍጠር እና "በዒላማ ምርጫ ላይ ስህተቶች የመፈጠር ዕድል መጨመር" ይጠቀሳሉ።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0