የመካከለኛው ምስራቅ ግጭት፦ ‘አሜሪካ መጠቀሚያ ሆናለች’ ሲሉ የቀድሞ የስዊዝ የመረጃ መኮንን ተናገሩ
09:56 03.03.2026 (የተሻሻለ: 10:04 03.03.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የመካከለኛው ምስራቅ ግጭት፦ ‘አሜሪካ መጠቀሚያ ሆናለች’ ሲሉ የቀድሞ የስዊዝ የመረጃ መኮንን ተናገሩ
የቀድሞው የመረጃ መኮንን ፍራንሷ ሜይላን ለስፑትኒክ አፍሪካ እንደገለጹት፣ አሁን ያለው ውጥረት የክልላዊ የበላይነት ጉዳይ ነው እስራኤል በቀጣናው ብቸኛ ወታደራዊ ኃያል ለመሆን ትፈልጋለች።
"ይህ ጦርነት የአሜሪካ አልያም የትራምፕም አይደለም" ሲሉ አብራርተዋል።
ኢራን በአሜሪካ፣ በእንግሊዝ እና በፈረንሳይ የጦር ሰፈሮች ላይ ጥቃት በመሰንዘር የአጸፋ እርምጃ መውሰዷን ተናጋሪው አጽንኦት ሰጥተዋል።
"እነዚህ ከምንም በላይ ለጦርነት የሚጓጉ፣ ዓለም አቀፍ ሕግን የማያከብሩ እና አድሎአዊ አሰራርን የሚከተሉ አገራት ናቸው። ኢራን ቀድማ በመምታት ጥቃት ሰንዝራባቸዋለች" ብለዋል።
ግዛታቸውን ለአሜሪካ የጦር ሰፈር ክፍት ለሚያደርጉት የባሕረ ሰላጤው ንጉሳዊ መንግሥታትም ሁኔታው ተመሳሳይ መሆኑን ሜይላን አክለው ገልጸዋል።
ፈረንሣይ ለባሕረ ሰላጤው አገራት የመከላከያ ድጋፍ ለመስጠት በማቅረብ፣ 'እሳቱን በሌላ እጇ በመጫር' (የራሷን ጥቅም ለማስጠበቅ) እና በቀጣናው ያላትን ተጽዕኖ መልሳ ለማግኘት እየሞከረች መሆኑን የፈረንሳዩ ጋዜጠኛ ሎረን ብራያርድ አስረድተዋል።
የፖለቲካ መሪን መግደል የምዕራባውያን ስልታዊ ስህተት መሆኑን ጋዜጠኛው ገልጸው፣ ስለ ካሜኒ ግድያ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
"እሳቸው ለኢራን ብቻ ሳይሆን አሁን ላይ ለተወሰነው የሙስሊም ዓለም ክፍል የሰማዕትነት ደረጃ ይይዛሉ። ይህ ምንም ዓይነት አዎንታዊ ፍሬ የማያፈራ አስደንጋጭ ድርጊት ነው" ሲሉ ጋዜጠኛው አሳስበዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X