"የዓድዋ ድል በመላው አፍሪካ የነፃነት ትግል መነሻ ሆኗል" ላቭሮቭ

© telegram sputnik_ethiopia"የዓድዋ ድል በመላው አፍሪካ የነፃነት ትግል መነሻ ሆኗል" ላቭሮቭ
የዓድዋ ድል በመላው አፍሪካ የነፃነት ትግል መነሻ ሆኗል ላቭሮቭ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 02.03.2026
ሰብስክራይብ

"የዓድዋ ድል በመላው አፍሪካ የነፃነት ትግል መነሻ ሆኗል" ላቭሮቭ

የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ለኢትዮጵያ አቻቸው ለ130ኛው የዓድዋ ድል በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ሰርጌ ላቭሮቭ፣ "የዓድዋ ጦርነት በዓለም ዙሪያ ሰፊ የማስተጋባት አቅም የነበረው ሲሆን፤ አንድ የአፍሪካ ሃገር በቅኝ ገዥ ኃይል ላይ የተቀዳጀው የመጀመሪያው ድል ነው። ይህ ታሪካዊ ክስተት የኢትዮጵያ ህዝብ ያለውን የመንፈስ ጥንካሬ ማረጋገጥ ብቻ ሳይሆን፣ በመላው አፍሪካ የነፃነት ትግል መነሻ ሆኗል" ሲሉ ተናግረዋል።

ሩሲያ እና ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግሥታት፣ በብሪክስ እና በሌሎች ዓለም አቀፍ ተቋማት ውስጥ በሚያደርጉት የጋራ ጥረት፣ "በባለብዙ ወገን ተዋናይነት እና በዓለም አቀፍ ሕግ የበላይነት ላይ የተመሠረተ ፍትሐዊ የዓለም ስርዓት እንዲሰፍን ቅድመ ሁኔታዎችን እየፈጠሩ ነው" ሲሉ የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገልጸዋል።

​በተጨማሪም በንግድ፣ በኢኮኖሚ፣ በሳይንስ፣ በባህል እና በሰብአዊ መስኮች እያደገ የመጣውን የሁለቱን ሀገራት ትብብር አድንቀዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0