ኬንያ እስከ ቀጣዩ ዓመት ድረስ 3,200 ትምህርት ቤቶችን የፀሐይ ኃይል ተጠቃሚ ታደርጋለች - ዊሊያም ሩቶ

ሰብስክራይብ

ኬንያ እስከ ቀጣዩ ዓመት ድረስ 3,200 ትምህርት ቤቶችን የፀሐይ ኃይል ተጠቃሚ ታደርጋለች - ዊሊያም ሩቶ

​በ260 ትምህርት ቤቶች ላይ የተደረገው የሙከራ መርሃ ግብር ስኬትን ተከትሎ፣ የኬኒያው ፕሬዝዳንት እንዳስታወቁት፤ 349,000 ዶላር የሚፈጀው ይህ ዕቅድ ለምግብ ማብሰያ፣ ለብርሃን እና ለሌሎች ፍላጎቶች የሚውለውን የእንጨት አጠቃቀም በፀሐይ ኃይል ለመተካት ያለመ ነው።

እንቅስቃሴው በመንግሥት ተቋማት ውስጥ ታዳሽ ኃይልን እና ለአየር ንብረት ተስማሚ የሆኑ መሠረተ ልማቶችን ለማስፋፋት የሚደረገው ሰፊ ጥረት አካል ነው። ​

እንደ ፕሬዝዳንቱ ገለጻ፣ የዚህ ዕቅድ ዓላማዎች፦

🟠 የኬንያን የካርቦን ልቀትን መቀነስ፤

🟠 የዕንጨትና ከሰል አጠቃቀምን መቀነስ እና

🟠 በትምህርት ዘርፍ የአረንጓዴ ኃይል አጠቃቀምን ማበረታታት ናቸው።

​የፀሐይ ኃይል ፕሮጀክቱ 780 ሜጋ ዋት ኃይል ያመነጫል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፣ ከትምህርት ቤቶች የሚተርፈው ኃይል ወደ ብሔራዊ የኤሌክትሪክ መስመር እንዲገባ ይደረጋል ሲሉ ሩቶ ተናግረዋል።

​ ዕቅዱ ስኬታማ ከሆነ፣ ትምህርት ቤቶች ለምግብ ማብሰያ በማገዶ እንጨትና በከሰል ላይ ያላቸውን ጥገኝነት የሚቀንስ ሲሆን፣ የኃይል አቅርቦት እጥረት ላለባቸው ተቋማትም የኤሌክትሪክ ወጪን ይቀንሳል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0