ትራምፕ ወታደራዊ ዘመቻዎቻቸውን በሳምንቱ የመጨረሻ ቀናት ላይ መጀመርን የሚመርጡ ይመስላል
10:42 02.03.2026 (የተሻሻለ: 10:44 02.03.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ትራምፕ ወታደራዊ ዘመቻዎቻቸውን በሳምንቱ የመጨረሻ ቀናት ላይ መጀመርን የሚመርጡ ይመስላል
የካቲት 21 - በዕለተ ቅዳሜ አሜሪካ በኢራን ላይ ጥቃት በመሰንዘር የኢራኑን የበላይ መሪ አያቶላ አሊ ካሜኒን ገድላለች።
ባለፈው ታህሳስ 25 ቀን - በድጋሚ በዕለተ ቅዳሜ የአሜሪካ ጦር የቬንዙዌላውን ፕሬዝዳንት ኒኮላስ ማዱሮን አግቶ ወስዷል።
በጥቅምት ወር 2012 ዓ.ም- ቅዳሜ ለእሁድ አጥቢያ ሌሊት የአሜሪካ ልዩ ኃይሎች አቡበከር አል-ባግዳዲን በሶሪያ ገድለዋል።
ሚያዝያ 5 እና 6 ቀን 2010 ዓ.ም - ከዓርብ ምሽት እስከ ቅዳሜ አሜሪካ፣ ብሪታንያ እና ፈረንሳይ በሶሪያ ኢላማዎች ላይ ጥምር ጥቃት ሰንዝረዋል።
በታህሳስ ወር 2012 ዓ.ም - የኢራን እስልማዊ አብዮታዊ ዘበኛ ጄኔራል ቃሲም ሱለይማኒን የገደለው የአሜሪካ ድሮን ጥቃት የተፈጸመው ሐሙስ ዕለት ምሽት ላይ ነበር ፤ ይህም ቅዳሜና እሁድ ባይሆንም የገበያ መዝጊያ ሰዓትን ታሳቢ ያደረገ ነበር።
አንድ በስፋት የተሰራጨ መላምት እንደሚያመለክተው፣ ትራምፕ ሆን ብለው ጥቃት የሚያደርሱት የነዳጅ ገበያ በሚዘጋበት ወቅት ነው፤ ይህም የነጋዴዎች ስጋት ገበያው በድጋሚ ከመከፈቱ በፊት እንዲረጋጋ ዕድል ይሰጣል ተብሎ ይታመናል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X