የአያቶላህ አሊ ካሜኒን የሞት ዜና ሞስኮ በብርቱ ተቃውሞና ጥልቅ ሃዘን ተቀብልዋለች - የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
18:35 01.03.2026 (የተሻሻለ: 18:44 01.03.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የአያቶላህ አሊ ካሜኒን የሞት ዜና ሞስኮ በብርቱ ተቃውሞና ጥልቅ ሃዘን ተቀብልዋለች - የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኢራን ዙሪያ ስላለው ሁኔታ የሰጣቸው ሌሎች መግለጫዎች፦
ሩሲያ በፖለቲካዊ ምክንያት የሚፈጸሙ ግድያዎችን እና የሉዓላዊ ሃገራት መሪዎችን በታለመ ሁኔታ የመግደል ድርጊትን በጥብቅ ታወግዛለች።
የሃገር መሪዎችን መግደል በሃገራት መካከል ያለውን ግንኙነት ከሚመሩ መርሆዎች ጋር የሚጋጭ እና ዓለም አቀፍ ሕግን በከፍተኛ ሁኔታ መጣስ ነው።
ሩሲያ፣ በኢራን ዙሪያ ያለው ውጥረት በአስቸኳይ እንዲረግብ፣ አፋጣኝ የተኩስ አቁም እንዲደረግ እና ወደ ፖለቲካዊና ዲፕሎማሲያዊ ሂደቶች እንዲመለሱ ጥሪ ታቀርባለች።
በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል የሚደረግ የባህር ላይ ትራንስፖርት መቋረጥ የዓለምን የነዳጅ እና የጋዝ ገበያ የማናጋት አደጋ አለው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X