ኢትዮጵያ ማንኛውንም ዓይነት አካላዊ ቅጣትን የሚከለክል ታሪካዊ የሕፃናት ሕግ አረቀቀች
16:59 01.03.2026 (የተሻሻለ: 17:04 01.03.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ ማንኛውንም ዓይነት አካላዊ ቅጣትን የሚከለክል ታሪካዊ የሕፃናት ሕግ አረቀቀች
ረቂቅ ሕጉ በአካላዊ ቅጣት ፋንታ ወላጆች፣ መምህራንና አሳዳጊዎች "አዎንታዊ የሥነ-ምግባር" እና የምክር ዘዴዎችን እንዲከተሉ ሕጉ ያዛል።
በሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ የሕፃናት መብትና ጥበቃ መሪ ሥራ አስፈጻሚ ዘቢደር ቦጋለ፣ አዲሱ አዋጅ ቀደም ሲል በሕግ ክፍተት የነበረባቸውን እንደ ሳይበር ጥቃት እና በቴክኖሎጂ የታገዙ በሕፃናት ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን ትኩረት ሰጥቶባቸዋል ሲሉ ተናገረዋል።
ረቂቅ ሕጉ "የሕፃናት የላቀ ጥቅም" በሚለው መርህ ላይ የተመሠረተ ነው ተብሏል፡፡ ማንኛውም የፍትሕ፣ የሕግ አውጪና የሃይማኖት ተቋማት ከቤተሰብ ፍላጎት በተለየ መልኩ ለሕፃኑ ደኅንነት ቅድሚያ እንዲሰጡ ያስገድዳል ሲሉ የሃገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X