የዓድዋ ድል “ለዓለም የአፍሪካ ዘር ሕዝብ የኩራት፣ የነፃነት እና የክብር ምልክት ሆኗል" - የኬንያ ባለሥልጣን
15:50 01.03.2026 (የተሻሻለ: 15:54 01.03.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የዓድዋ ድል “ለዓለም የአፍሪካ ዘር ሕዝብ የኩራት፣ የነፃነት እና የክብር ምልክት ሆኗል" - የኬንያ ባለሥልጣን
“ታላቅ ታሪክ ለብሩህ ተስፋ” በሚል መሪ ቃል በናይሮቢ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በተከበረው 130ኛውን የዓድዋ ድል በዓል ላይ የክብር እንግዳ ሆነው የተገኙት የኬንያ ሪፐብሊክ የጠቅላይ ካቢኔ ፀሐፊ እና የውጭና የዲያስፖራ ጉዳዮች ካቢኔ ፀሐፊ ሙሳሊያ ሙዳቫዲ ናቸው።
የዓድዋ ድል፣ “ለኢትዮጵያ ታሪክ ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካና ለቀሪው ዓለምም ጭምር ወሳኝ የታሪክ ምዕራፍ ነው” ሲሉ የክብር እንግዳው በመድረኩ ላይ ንግግር አድርገዋል።
በኬንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ጄነራል ባጫ ደበሌ በበኩላቸው፣ የዓድዋ ድል ወታደራዊ ድል ብቻ ሳይሆን አፍሪካውያን በጭቆና ላይ ያሳዩት የጽናት መግለጫ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።
አክለውም፣ ድሉ ለተጨቆኑ ሕዝቦች የተስፋ ብርሃን እና ለፓን-አፍሪካኒዝም እንቅስቃሴ መሰረት መሆኑንም ገልጸዋል።
በዕለቱም፣ የኢትዮጵያ ባህላዊና የኪነ-ጥበብ ስራዎች በ"ኪን - ኢትዮጵያ" የባህል ቡድን አማካኝነት መቅረቡን ኤምባሲው አስታውቋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X