በ2017/18 የምርት ዘመን 70 ሺህ ሚትሪክ ቶን ጥጥ ተመርቷል - የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ
11:25 01.03.2026 (የተሻሻለ: 11:34 01.03.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በ2017/18 የምርት ዘመን 70 ሺህ ሚትሪክ ቶን ጥጥ ተመርቷል - የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ
በምርት ዘመኑ በአጠቃላይ110 ሺህ መሬት በጥጥ ምርት መሸፈኑን የጥጥ ምርትን አስመልክቶ በተደረገ ሃገራዊ መድረክ ላይ ተገልጿል።
የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ሀሰን መሐመድ እንደተናገሩት፣ ኢትዮጵያ ለጥጥ ልማት ተስማሚ ከባቢ ቢኖራትም በሚገባ አልምቶ ከዘርፉ የሚጠበቀውን ጥቅም ማግኘት አልተቻለም።
ከጥጥና ጨርቃጨርቅ ዘርፍ ኢትዮጵያ ማግኘት ያለባትን ጥቅም እንድታገኝ በዘላቂነት ዘርፉን በመደገፍ ምርትና ምርታማነቱን ማሳደግ ይገባል ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያ ለጥጥ ልማት የተመቸ የእርሻ መሬት ቢኖራትም አሁን እየተመረተ ያለው ከ5 በመቶ በታች መሆኑን የተጠቀሰ ሲሆን ግብርና ሚኒስቴርና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በቅንጀት መሥራት እንደሚገባቸው ተነስቷል፡፡
ቪዲዮ፦ ከግብርና ሚኒስቴር የማኅበራዊ ሚዲያ ገጽ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X