የአሜሪካ እና የእስራኤል ጥቃት በኢራን፦ የቅርብ ጊዜ መረጃዎች

የአሜሪካ እና የእስራኤል ጥቃት በኢራን፦ የቅርብ ጊዜ መረጃዎች
◻ የኢራን መንግሥት መገናኛ ብዙኃን የሀገሪቱ የበላይ መሪ አያቶላህ አሊ ካሜኒ በዋና ከተማዋ ቴህራን በሚገኘው መኖሪያ ግቢያቸው ውስጥ መገደላቸውን አረጋግጠዋል።
◻ እንደ ቀይ ጨረቃ መረጃ፣ በአሜሪካ እና በእስራኤል የጥቃት እርምጃ እስካሁን ከ200 በላይ ሰዎች ተገድለዋል።
◻ የእስራኤል ጦር በኢራን እስላማዊ ሪፐብሊክ ውስጥ በሚገኙ 30 አካባቢዎች ላይ አዲስ ተከታታይ ጥቃቶችን ሰንዝሯል።
◻ በደቡብ ኢራን በሚናብ ከተማ በሚገኝ የሴቶች ትምህርት ቤት ላይ በተሰነዘረው ጥቃት የሟቾች ቁጥር ወደ 118 ከፍ ብሏል።
◻ የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ በእስራኤል እና በቀጣናው በሚገኙ የአሜሪካ ጦር ሰፈሮች ላይ "ስድስተኛውን ዙር" የሚሳኤል እና የድሮን የመልሶ ማጥቃት እርምጃ ወስዷል።
◻ ኢራን፣ በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ በሚገኙ ሁለት አየር ማረፊያዎች እና በአንድ የኩዌት አየር ማረፊያ ላይ ጥቃት ካደረሰች በኋላ፣ በባህሬን ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ላይም በድሮን ጥቃት ጉዳት አድርሳለች።
◻ በኢራቅ የሚገኘው እና የአሜሪካ ወታደሮች ሰፈር የሆነው የኤርቢል አየር ኃይል ጣቢያ ላይ የኢራኑ ፋርስ የዜና ወኪል ከፍተኛ ፍንዳታ መከሰቱን ከዘገበ በኋላ፣ ትልቅ የጥቁር ጭስ ደመና ታይቷል።
መግለጫዎች
የኢራን አብዮታዊ ዘብ፣ በአያቶላህ አሊ ካሜኒ ሞት ምክንያት "በኢራን ጦር ኃይል ታሪክ ውስጥ እጅግ አስከፊው የማጥቃት እርምጃ" መጀመሩን አስታውቋል።
የካሜኒ ግድያ "ትልቅ ወንጀል" ነው ያለው የኢራን ፕሬዝዳንት ጽሕፈት ቤት፣ ድርጊቱ "የራሱ ምላሽ ይኖረዋል" ሲል አስጠንቅቋል። "ይህንን ወንጀል ያቀነባበሩትን እና የፈጸሙትን እንዲጸጸቱ እናደርጋለን" ሲልም ዝቷል።
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራን ምላሽ ለመስጠት ከሞከረች የበለጠ ጠንካራ ጥቃት እንደሚሰነዘርባት አስጠንቅቀዋል።
የኢራን ፓርላማ አፈ ጉባኤ መሐመድ ባገር ጋሊባፍ፣ ኢራን ለአሜሪካ እና እስራኤል ጥቃት ዝግጁ መሆኗን ገልጸው፣ "ከበላይ መሪው ሞት በኋላ ለሚከሰቱ ማናቸውም ሁኔታዎች ራሳችንን አዘጋጅተናል" ብለዋል።
በተመድ የሩሲያ ቋሚ ተወካይ ቫሲሊ ኔቤንዚያ፣ የአሜሪካ እና የእስራኤል የጦርነት እርምጃ "የዲፕሎማሲ ክህደት" ነው ሲሉ ወቅሰዋል።
በተመድ የኢራን ቋሚ ተወካይ አሚር ሰኢድ ኢራቫኒ፣ ሩሲያ፣ ቻይና እና ፓኪስታን የአሜሪካን እና የእስራኤልን "ሕገ-ወጥ የወታደራዊ ጥቃት እርምጃ" በማውገዛቸው ምስጋና አቅርበዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X