'አሜሪካ የአረብ ሀገራትን ወራለች' - የኢራን ፓርላማ አባል
19:28 28.02.2026 (የተሻሻለ: 19:34 28.02.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
'አሜሪካ የአረብ ሀገራትን ወራለች' - የኢራን ፓርላማ አባል
ኢራን፤ በግዛታቸው ላይ የሚገኙ የአሜሪካ ጦር ሠፈሮችን ከማጥቃቷ በፊት፤ ሁሉንም ሀገራት በቅድሚያ አስጠንቅቃለች ሲሉ የኢራን ፓርላማ የብሔራዊ ደህንነት እና ዓለም አቀፍ ፖሊሲ ኮሚሽን ምክትል ኃላፊ አባስ ሞቅታዳኢ ለስፑትኒክ ገልጸዋል።
"የኢራን እርምጃ ከዓለም አቀፍ ሕግ ጋር የተጣጣመ እና ሕጋዊ ራስን የመከላከል መብት ነው" ሲሉ በመካከለኛው ምስራቅ በሚገኙ የአሜሪካ ጦር ሠፈሮች ላይ ኢራን ለፈጸመችው ጥቃት የቀጣናው ሀገራት ለሰጡት ምላሽ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
አሜሪካ የተመድ የፀጥታው ምክር ቤት ፕሬዚዳንትነትን በቅርቡ የምትረከብ መሆኑ "ታላቅ ምፅት" ነው ሲሉም አክለዋል።
"ሰላም እና ዓለም አቀፍ ደህንነትን ለመጠበቅ ግንባር ቀደም ሚና ይጫወታል ተብሎ የሚጠበቀው የፀጥታው ምክር ቤት፤ አሁን በጠብ አጫሪ እና የሕዝቦችንና የሀገራትን መብትና ደህንነት ወደ ጎን በሚል ሀገር ይመራል።"
በቀጠናው የሚገኝ ማንኛውም ቋሚም ሆነ ተንቀሳቃሽ የአሜሪካ ኢላማ ለኢራን ሕጋዊ ወታደራዊ ግብ ነው ብለዋል።
ቴህራን "በዓለም ጠንካራ የተባለው ጦር ኢራን ላይ ብርቱ እና የበላይ ለመሆን የሚያስችል በቂ ጥንካሬ እንደሌለው" ታሳያለች ሲሉ አፅንዖት ሰጥተው ተናግረዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X