የአሜሪካ ጤናን በማዕድን የሚለውጠው ስምምነት ዚምባብዌን ዝቅ የሚያደርግ ነው - ፖለቲከኛ
19:11 28.02.2026 (የተሻሻለ: 19:14 28.02.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የአሜሪካ ጤናን በማዕድን የሚለውጠው ስምምነት ዚምባብዌን ዝቅ የሚያደርግ ነው - ፖለቲከኛ
ፕሬዚዳንት ኤመርሰን ምናንጋጓ ከአሜሪካ ጋር የተጀመረው "ማዕድናትን ለጤና በጀት" ስምምነት እንዲቆም ማድረጋቸው ትክክለኛ ውሳኔ ነው ሲሉ የዛኑ ፒኤፍ ቃል አቀባይ እና የቀድሞው የካቢኔ ሚኒስትር አምባሳደር ክሪስቶፈር ሙትስቫንግዋ ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልጸዋል።
ስምምነቱ ለአሜሪካ ያጋደለ እና ለልውውጥ የቀረቡትን ነገሮች ትክክለኛ ዋጋ ያላገናዘበ ነው ሲሉም ሞግተዋል።
አምባሳደር ሙትስቫንግዋ ዚምባብዌ ከዚህ ይልቅ ብረታ ብረት ወደ አሜሪካ ብትልክ የተሻለ መሆኑን ጠቁመዋል። አሜሪካ በዓለም ትልቋ የብረት ገበያ በመሆኗ የዚምባብዌን የማምረት አቅም በአግባቡ ለመጠቀም ያስችላል ብለዋል።
እንደ እሳቸው ገለፃ ይህ አካሄድ የሚከተሉትን ጥቅሞች ያስገኛል፦
◻ የሀገር ውስጥ የማዕድን ውጤቶችን ማበልጸግ፣
◻ የተሟላ የእሴት ሰንሰለት መገንባት፣
◻ የበለጠ ሚዛናዊ የሆነ አጋርነት መፍጠር።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X