ጎረቤት ሀገር ኬንያ የ "ኪን ኢትዮጵያ" የጥበብ ቡድን ቀጣይ መዳረሻ መሆኗ ተገለፀ
17:33 28.02.2026 (የተሻሻለ: 17:34 28.02.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ጎረቤት ሀገር ኬንያ የ "ኪን ኢትዮጵያ" የጥበብ ቡድን ቀጣይ መዳረሻ መሆኗ ተገለፀ
የጥበብ ጉዞው 130ኛውን የዓድዋ በዓል መነሻ በማድረግ እንደሚካሄድና የድሉን አፍሪካዊነት ከማንበር ባለፈ በዓይነቱ የመጀመሪያው እንደሚሆን ባሕልና ስፖርት ሚኒስቴር አስታውቋል።
የባሕል ቡድኑ "ኪን ኢትዮጵያ የኢትዮጵያ ማንሰራራት ብስራት" በሚል መሪ ቃል፤ ቀደም ሲል ሩሲያን ጨምሮ በቻይና እና በጃፓን በተካሄዱ ስምንት መድረኮች የሀገርን ጥበብ፣ ባሕል፣ ታሪክ እና የከፍታ ዘመን ግስጋሴ ለዓለም እንዳስተዋወቀ የባሕልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ ነብዩ ባዬ አስታውሰዋል።
ቪዲዮው ኪን-ኢትዮጵያ የባሕል ቡድን በሩሲያ ሴንት ፒተርስበርግ ከተማ በአሌክስ አንደርስኪ ቴዓትር ያቀረበውን የሙዚቃ ዝግጅት ያሳያል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X