የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሜሪካ እና አስራኤል በኢራን ላይ የከፈቱት ጦርነት እንዳይሰፋ በማስጠንቀቅ፤ በ “ወንድም የአረብ ሀገራት” ላይ የተፈጸሙ ጥቃቶችን ኮነነ
17:18 28.02.2026 (የተሻሻለ: 17:24 28.02.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሜሪካ እና አስራኤል በኢራን ላይ የከፈቱት ጦርነት እንዳይሰፋ በማስጠንቀቅ፤ በ “ወንድም የአረብ ሀገራት” ላይ የተፈጸሙ ጥቃቶችን ኮነነ
ሚኒስቴሩ በመግለጫው ያነሳቸው ተጨማሪ ሃሳቦች፦
◻ ግብፅ በቀጣናው እየታየ ያለው ወታደራዊ መካካር እጅግ እንዳሰጋት ትገልጻለች።
◻ ካይሮ የግጭት ቀጣናው መስፋፋት በሚያስከትለው አደጋ እና በክልላዊና ዓለም አቀፋዊ ሰላም እና መረጋጋት ላይ የሚፈጥረውን ተፅዕኖ በተመለከተ ታስጠነቅቃለች።
◻ "ወታደራዊ መፍትሄዎች ተጨማሪ ግጭት ብቻ ነው የሚያመጡት፡፡ ቀውሱን ለመቆጣጠር ብቸኛው መንገድ ፖለቲካዊ እና ዲፕሎማሲያዊ መፍትሄዎች ናቸው።"
◻ ግብፅ በተጨማሪም በወንድም የአረብ ሀገራት ማለትም በኳታር፣ በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች፣ በኩዌት፣ በባህሬን እና በዮርዳኖስ ግዛቶች ላይ የተፈጸሙትን ጥቃቶች ትኮንናለች።
◻ እነዚህ ድርጊቶች በአረብ ሀገራት እና በአጠቃላይ በቀጣናው ደህንነት እና መረጋጋት ላይ ከፍተኛ አደጋ ይደቅናሉ።
◻ ግብፅ የግጭቱ አድማስ እንዳይሰፋ እና ሉዓላዊነት እንዲከበር ጥሪ ታቀርባለች።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X