የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ከሰባተኛው አጠቃላይ ምርጫ ጋር ተያይዞ በዋትስአፕ መጠነ ሰፊ የሳይበር ጥቃት እየተፈጸም ነው ሲል አስጠነቀቀ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ከሰባተኛው አጠቃላይ ምርጫ ጋር ተያይዞ በዋትስአፕ መጠነ ሰፊ የሳይበር ጥቃት እየተፈጸም ነው ሲል አስጠነቀቀ
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ከሰባተኛው አጠቃላይ ምርጫ ጋር ተያይዞ በዋትስአፕ መጠነ ሰፊ የሳይበር ጥቃት እየተፈጸም ነው ሲል አስጠነቀቀ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 28.02.2026
ሰብስክራይብ

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ከሰባተኛው አጠቃላይ ምርጫ ጋር ተያይዞ በዋትስአፕ መጠነ ሰፊ የሳይበር ጥቃት እየተፈጸም ነው ሲል አስጠነቀቀ

የጥቃት ዘመቻው በተለይ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችን፣ በውጭ ሀገር የሚኖሩ ተማሪዎችን፣ በበይነመረብ ትምህርታቸውን የሚከታተሉ ግለሰቦችን እና ታዋቂ ሰዎችን ኢላማ ያደረገ በመሆኑ ማኅበረሱ ጥንቃቄ እንዲያደርግ አሳስቧል፡፡

የመረጃ መንታፊዎቹ፣ የፖለቲካ ፓርቲ ደጋፊ በመምሰልና የፓርቲዎችን አርማ በመጠቀም፤ “ይህንን ሊንክ በመጫን ለፓርቲያችን ያለዎትን ድጋፍ ይግለጹ” ወይም “የምርጫ ቅስቀሳ ቡድናችንን ይቀላቀሉ” የሚሉ አሳሳች መልዕክቶችን በመላክ የግለሰቦችን አካውንት እንደሚጠልፉ አስተዳደሩ በማሳያነት ጠቅሷል።

አስተዳደሩ ኅብረተሰቡ ባለሁለት ደረጃ ማረጋገጫን እንዲጠቀም፣ የማረጋገጫ ኮዶችን በማንኛውም ሁኔታ ለማንም አሳልፎ ከመስጠት እንዲቆጠብ፣ አጠራጣሪ ሊንኮችን ከመንካት እንዲታቀብ እና የገንዘብ ጥያቄዎች ሲቀርቡ በቀጥታ ስልክ በመደወል እንዲያረጋግጥ መክሯል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0