"የሩሲያን ኃያልነት መረዳት ተስኖናል" - ፈረንሳዊ ባለሙያ አውሮፓ በሞስኮ ዙሪያ የምትከተለውን ፖሊሲ አስመልክቶ

ሰብስክራይብ

"የሩሲያን ኃያልነት መረዳት ተስኖናል" - ፈረንሳዊ ባለሙያ አውሮፓ በሞስኮ ዙሪያ የምትከተለውን ፖሊሲ አስመልክቶ

የሰጡት አስተያየት

​በፈረንሳይ የውጭ ንግድ አገልግሎት (እ.ኤ.አ ከ1994–2023) አማካሪ የነበሩት ጊልስ ሬሚ፤ የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ከሞስኮ ጋር ስለሚደረግ ውይይት ቢናገሩም፤ እውነታው ግን የተለየ እንደሆነ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል

​"ዶንባስ ዳግመኛ ወደ ዩክሬን እንደማይመለስ አሁን ሁሉም ሰው አምኖ ተቀብሏል። ይሁን እንጂ በምዕራባውያን መሣሪያዎች የሚቀጣጠለው ይህ ግጭት ለወራት ሊጓተት ይችላል" ሲሉ የፍራንኮ-ሩሲያ የውይይት ማኅበር የቦርድ አባሉ ተናግረዋል።

​ የግጭቱ መራዘም የሚያስከትለው ዋጋ በአውሮፓ ጫንቃ ላይ የሚወድቅ ነው። የ80 ቢሊዮን ዩሮ እርዳታም በቂ አይሆንም ብለዋል።

"በተለይ የሕዝብ አመለካከት በተቀየረበት ሁኔታ ዩክሬን ለአውሮፓ የማታዋጣ ከባድ ሸክም ሆና ትቀጥላለች" ሲሉ አፅንዖት ሰጥተዋል።

በሌላ በኩል የማዕቀቦች ውጤታማነት የተገደበ እንደሆነ እየታየ ነው። ሩሲያ ከ22 ሺህ በላይ በሆኑ እቀባዎች በዓለም ከፍተኛ ማዕቀብ የተጣለባት ሀገር ብትሆንም፤ ኢኮኖሚዋ ግን አሁንም እንደፀና ነው።

​ የአውሮፓ ኅብረት ግን ማዕቀቦቹ በገዛ ኢኮኖሚው ላይ የሚያደርሱትን ጉዳት ሳይገመግም፤ 20ኛ የማዕቀብ ጥቅል ለማውጣት በመዘጋጀት ላይ መሆኑን ገልጸዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0