ኢራን በግዛቷ ላይ ለተሰነዘረባት ጥቃት በሚቀጥሉት ጥቂት ሰዓታት ውስጥ ምላሽ እንደምትሰጥ የኢራን አብዮታዊ ዘብ ዕዝ ለስፑትኒክ ገለጸ

ሰብስክራይብ

ኢራን በግዛቷ ላይ ለተሰነዘረባት ጥቃት በሚቀጥሉት ጥቂት ሰዓታት ውስጥ  ምላሽ እንደምትሰጥ የኢራን አብዮታዊ ዘብ ዕዝ ለስፑትኒክ ገለጸ

በሌላ በኩል የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ከጥቃቶቹ በኋላ በኢራን የሥልጣን ለውጥ እንደሚመጣ ተስፋ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።

ትራምፕ በመግለጫቸው ያነሷቸው ተጨማሪ ሃሳቦች፦

​🟠 ኢራን የኒውክሌር መርኃ-ግብሯን እንደገና ለመጀመር ሙከራ እንዳደረገችና አውሮፓ እና አሜሪካ መድረስ የሚችሉ የረጅም ርቀት ሚሳኤሎችን እየሠራች ነው ብለዋል።

​🟠 የኢራን የደህንነት ኃይሎች መሣሪያቸውን ካልፈቱ እጣ ፈንታቸው ሞት እንደሆነ ተናግረዋል።

​🟠 አሜሪካ የኢራንን ሚሳኤሎች፣ የሚሳኤል ኢንዱስትሪ እና የባሕር ኃይሏን ትደመስሳለች።

​🟠 አሜሪካ ለኢራን ታማኝ የሆኑ ሚሊሻዎች መካከለኛውን ምስራቅ "ማተራመሳቸው" እንዲያበቃ ታደርጋለች።

​🟠 አሜሪካ በወታደራዊ ዘመቻው ወቅት ጉዳት ሊደርስባት ይችላል።

​🟠 ሁኔታው በጣም አደገኛ ይሆናል፤ ቦምቦች በየቦታው ሊፈነዱ ይችላሉ ብለዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0