እንግሊዝ እና ፈረንሳይ በዩክሬን የኒውክሌር ዕቅዳቸው ቁስላቸውን ለመላስ እየሞከሩ ነው - ኢትዮጵያዊ ምሁር

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱእንግሊዝ እና ፈረንሳይ በዩክሬን የኒውክሌር ዕቅዳቸው ቁስላቸውን ለመላስ እየሞከሩ ነው - ኢትዮጵያዊ ምሁር
እንግሊዝ እና ፈረንሳይ በዩክሬን የኒውክሌር ዕቅዳቸው ቁስላቸውን ለመላስ እየሞከሩ ነው - ኢትዮጵያዊ ምሁር - Sputnik አፍሪካ, 1920, 27.02.2026
ሰብስክራይብ

እንግሊዝ እና ፈረንሳይ በዩክሬን የኒውክሌር ዕቅዳቸው ቁስላቸውን ለመላስ እየሞከሩ ነው - ኢትዮጵያዊ ምሁር

የሩሲያ የውጭ ደህንነት መሥሪያ ቤት ለንደን እና ፓሪስ ለዩክሬን የኒውክሌር አልያም "ቆሻሻ ቦምብ" ለማቅረብ እንዳቀዱ መግለጹን ተከትሎ ለስፑትኒክ አፍሪካ አስተያየታቸውን የሰጡት የዲላ ዩኒቨርስቲ መምህር ዳዊት መዝገበጸጋዬ፤ ሁለቱ ሀገራት በግጭቱ በርካታ ወታደራዊ አማካሪዎችን እንዳጡና እንዳንዶችም በሩሲያ ቁጥጥር ስር መግባታቸውን በመግለጽ፤ ከባድ ቁስል አለባቸው ብለዋል፡፡

“የበላይነት ስሜታቸው በጣም ተጎድቷል። ስለዚህ ይህን የመጨረሻ አማራጫቸው አድረገውታል።”

አክለውም ሀገራቱ ለሰላም ጥረቶች በተደጋጋሚ እንቅፋት ሲሆኑ መታየታቸውን ተናግረዋል፡፡

"እንግሊዝ እና ፈረንሳይ፤ አሜሪካንና የትራምፕ አስተዳደርን ጦርነቱ እንዲቀጥል ለማሳመን የሚችሉትን ሁሉ ሞክረዋል፡፡ ነገር ግን ይህ ጦርነት ባለበት ሊቀጥል አይችልም፡፡"

በሌላ በኩል በተጋለጠባቸው ዕቅድ በዩክሬን በኩል የሚደርስባቸውን ከባድ ሽንፈት ለመከላከል ጥረት እያደርጉ ሊሆን እንደሚችል ጠቁመዋል፡፡

“በዩክሬን አመራር ወታደራዊ አቅም ላይ እምነት አጥተዋል። ስለዚህ የመጨረሻ ትኬታቸው ዩክሬንን በኒውክሌር ጦር መሣሪያ ማስታጠቅ ነው። ይህ የሚያሳየው በሩሲያ ስልታዊ ወታደራዊ ሽንፈት ሊደርስባቸው እንደሆነ መገንዘባቸውን ነው።”

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0