ኃያላን ሀገራት ችግሮችን ከመፍታት ይልቅ ውጥረት ማባባስን መርጠዋል - የጋና ፓርላማ አባል
18:25 27.02.2026 (የተሻሻለ: 18:34 27.02.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኃያላን ሀገራት ችግሮችን ከመፍታት ይልቅ ውጥረት ማባባስን መርጠዋል - የጋና ፓርላማ አባል
“ነገሩ ቅንጣት ታክል እንኳን እውነት ከሆነ ኃያላኖቹ እንግሊዝ እና ፈረንሳይ ይህን ከማድረግ ሊቆጠቡ ይገባል። ሩሲያ የዓለም ኃያላን ችግሩን ለመፍታት ከመሞከር ይልቅ እያባባሱት እንደሆነ ገልጻለች” ሲሉ የጋና ፓርላማ የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ አባል ጆሴፍ ክዋሜ ኩማህ፤ ምዕራባውያን ለኪየቭ የኒውክሌር መሣሪያዎችን ለማስተላለፍ ማቀዳቸውን አስመልክቶ ለስፑትኒክ አፍሪካ በሰጡት አስተያየት ተናግረዋል።
የሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት በስንዴ፣ በነዳጅ እና በጋዝ አቅርቦት ላይ በፈጠረው መስተጓጎል ምክንያት በዓለም አቀፍ ገበያዎች እና በማደግ ላይ ባሉ ኢኮኖሚዎች ላይ ሰፊ የኢኮኖሚ ጉዳት ማድረሱን ጠቁመዋል።
የቀድሞው ፕሬዚዳንት ናና አኩፎ-አዶ፤ ጦርነቱ ሩሲያ እና ዩክሬንን ብቻ እንደሚነካ ተደርጎ መታየት እንደሌለበት በማስጠንቀቅ፤ ዓለም አቀፋዊ ተጽዕኖው ላይ አጽንኦት መስጠታቸውን የፓርላማ አባሉ አክለዋል።
ኃያላኑ መፍትሄ ከመፈለግ ይልቅ ግጭቱን በሚያባብሱበት ምክንያት እና በእውነተኛ ፍላጎታቸው ዙሪያም ጥያቄ አንስተዋል።
አስተያየታቸው በተባበሩት መንግሥታት የሩሲያ መልዕክተኛ ቫሲሊ ኔቤንዚያ፤ እንግሊዝና ፈረንሳይ የኒውክሌር መሣሪያ ወይም “ቆሻሻ ቦምብ” ለዩክሬን ለማቅረብ አቅደዋል ሲሉ ክስ መሰንዘራቸውን ተከትሎ የመጣ ነው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X