የአፍሪካ የጤና መሪዎች በአሜሪካ የገንዘብ ድጋፍ ስምምነቶች ዙሪያ ስጋታቸውን ገለፁ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየአፍሪካ የጤና መሪዎች በአሜሪካ የገንዘብ ድጋፍ ስምምነቶች ዙሪያ ስጋታቸውን ገለፁ
የአፍሪካ የጤና መሪዎች በአሜሪካ የገንዘብ ድጋፍ ስምምነቶች ዙሪያ ስጋታቸውን ገለፁ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 27.02.2026
ሰብስክራይብ

የአፍሪካ የጤና መሪዎች በአሜሪካ የገንዘብ ድጋፍ ስምምነቶች ዙሪያ ስጋታቸውን ገለፁ

“ከመረጃ እና በሽታ አምጪ ተህዋስያንን ከማጋራት ጋር በተያያዘ ከፍተኛ ስጋቶች አሉ” ሲሉ የአፍሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያና መከላከያ ማዕከል ኃላፊ ዣን ካሴያ ተናግረዋል።

ዚምባብዌ ቁልፍ ከሆኑ የመረጃ ጉዳዮች እና ፍትሐዊ ካልሆኑ ውሎች ጋር በተያያዘ፤ ከአሜሪካ ጋር ልታደርገው የነበረውን የ367 ሚሊዮን ዶላር የአምስት ዓመት ስምምነት ውይይት ረቡዕ አቋርጣለች። ዛምቢያ በበኩሏ በረቂቅ ስምምነቱ በተካተቱ አንዳንድ ክፍሎች ላይ ተቃውሞዋን ገልጻለች።

ዓለም አቀፍ የጤና ተሟጋቾች፤ ዋሽንግተን ፈጣን የበሽታ አምጪ ተህዋስያን መረጃን ማጋራት ለገንዘብ ድጋፉ ቅድመ ሁኔታ አድርጋ ማቅረቧን ተችተዋል። እንደ መገናኛ ብዙኃን ዘገባ ከሆነ፤ በዚህ መረጃ መሠረት የሚመረቱ መድኃኒቶች ወይም ክትባቶች ለተጎዱ ሀገራት እንደሚደርሱ ምንም ዓይነት ዋስትና የለም።

ℹ ስምምነቶቹ የፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር የረድኤት ድርጅቶችን የገንዘብ ድጋፍ በማቋረጥ፤ “አሜሪካ ትቅደም” የሚለውን ፖሊሲ ተግባራዊ ካደርገ በኋላ የአሜሪካን የዓለም አቀፍ ጤና ፖሊሲ ለውጥ የሚያንጸባርቁ ናቸው።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0