የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን አገልግሎቱን ሙሉ በሙሉ ዲጂታል ማድረጉን አስታወቀ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን አገልግሎቱን ሙሉ በሙሉ ዲጂታል ማድረጉን አስታወቀ
የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን አገልግሎቱን ሙሉ በሙሉ ዲጂታል ማድረጉን አስታወቀ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 27.02.2026
ሰብስክራይብ

የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን አገልግሎቱን ሙሉ በሙሉ ዲጂታል ማድረጉን አስታወቀ

የጉምሩክ ኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር አዘዘው ጫኔ፤ ተቋሙ ነጋዴዎች በየትኛውም ቦታ ሆነው የሚጠበቅባቸውን የጉምሩክ ሂደት የሚፈጽሙበትን የዲጂታል አሠራር እንደዘረጋ ለሀገር ውስጥ ሚዲያ ገልጸዋል።

ከ70 በላይ ተቋማትን የሚያገናኝ የኤሌክትሮኒክ የአንድ መስኮት መድረክ የንግድ ሥራን እያቀላጠፈ እንደሚገኝም አክለዋል፡፡

በድንበር አካባቢዎች እስከ 50 ኪሎ ሜትር የሚሸፍኑ በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የታገዙ ካሜራዎች መተከላቸውን አያይዘው ገልፀዋል።

የኢ-ታክስ፣ የቅሬታ ማቅረቢያ እና የደረሰኝ ማረጋገጫ አገልግሎቶች በኦንላይን እንዲከናወኑ መደረጉም ተመላክቷል።

በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለጸገ ምሥል

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0