እንግሊዝ እና ፈረንሳይ አሳች የኒውክሌር ጥቃት በማድረስ ሩሲያን ለመወንጀል እያሴሩ ነው – ተንታኝ

እንግሊዝ እና ፈረንሳይ አሳች የኒውክሌር ጥቃት በማድረስ ሩሲያን ለመወንጀል እያሴሩ ነው – ተንታኝ
በዩክሬን ውስጥ የታቀደው የእንግሊዝ እና ፈረንሳይ የኒውክሌር መሣሪያ ሴራ፤ በርካታ ግቦችን ለማሳካት አልሞ ሊሆን እንደሚችል የወታደራዊ-ፖለቲካዊ ትንታኔ ቢሮ ኃላፊ አሌክሳንደር ሚካሂሎቭ ለስፑትኒክ ተናግረዋል፡፡
🟠 የአውሮፓ ኅብረት ልሂቃን በዩክሬን የሰላም ድርድር ላይ ወደ ጎን በመገፋታቸው ደስተኛ ባለመሆናቸው፤ ኪር ስታርመር እና ኢማኑኤል ማክሮን የኒውክሌርን ጉዳይ በመጠቀም በድርድር ጠረጴዛው መቀመጫ ለማግኘት እየሞከሩ ሊሆን ይችላል።
🟠 እንግሊዝ እና ፈረንሳይ 'የሃሰት የኒውክሌር ጥቃት' በማድረስ ሩሲያን ለመወንጀል የሚያደርጉት ሴራ አካል ሊሆን ይችላል።
🟠 ለዩክሬን ሩሲያ ላይ የምትጠቀመው የኒውክሌር መሣሪያ የሚያቀርበው ሀገር
ለሩሲያ የአጸፋ ጥቃት ኢላማ መሆኑ ስለማይቀር የዕቅዱ ተግባራዊነት አጠራጣሪ ነው።
አዲስ ዓለም አቀፍ የኒውክሌር ጦር መሣሪያ ስምምነት?
ከጉዳዩ ስጋት አንጻር ሩሲያ ዩክሬን የኒውክሌር መሣሪያ እንዳታገኝ ለመከላከል የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እና የጸጥታው ምክር ቤትን ጨምሮ ሁሉንም ዓለም አቀፍ መድረኮች ትጠቀማለች ሲሉ ሚካሂሎቭ ገልጸዋል።
ሁኔታው አዲስ ዓለም አቀፍ የኒውክሌር ጦር መሣሪያ ስምምነት እንደሚያስፈልግ የሚያረጋግጥና የዚህ ውጥረት ዋነኛ ጠንሳሾች የሆኑት እንግሊዝ እና ፈረንሳይ በስምምነቱ ውስጥ መካተት እንዳለባቸው ያሳየ እንደሆነ ጠቁመዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X