በኢትዮጵያ ፖሊስ ታሪክ የመጀመሪያው ነው የተባለ ዘመናዊ የኪነ-ጥበባት ማዕከል ሊገነባ ነው
19:51 26.02.2026 (የተሻሻለ: 19:54 26.02.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በኢትዮጵያ ፖሊስ ታሪክ የመጀመሪያው ነው የተባለ ዘመናዊ የኪነ-ጥበባት ማዕከል ሊገነባ ነው
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል፤ የህንፃ ግንባታ ማስጀመሪያ የመሠረት ድንጋዩን የካቲት 18 ቀን 2018 ዓ.ም አስቀምጠዋል።
ማዕከሉ በቀድሞው የፈጥኖ ደራሽ ካምፕ፤ በአሁኑ የፖሊስ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚገነባ ሲሆን የምህንድስና ሥራው ሙሉ በሙሉ በተቋሙ የራስ አቅም እንደሚከናወን ተገልጿል፡፡
ማዕከሉ ፖሊስ በፀጥታ ሥራው ላይ የኪነ-ጥበብን ጉልበት በመጠቀም ዘመናዊና ሥልጡን ተቋም ለመገንባት የሚያደርገውን ጥረት የሚያፋጥን ታሪካዊ ስኬት ነው ተብሏል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X