ናይጄሪያ በአሜሪካ የሚቀርብባትን ተደጋጋሚ የሐይማኖታዊ ጥቃት ክስ ውድቅ አደረገች

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱናይጄሪያ በአሜሪካ የሚቀርብባትን ተደጋጋሚ የሐይማኖታዊ ጥቃት ክስ ውድቅ አደረገች
ናይጄሪያ በአሜሪካ የሚቀርብባትን ተደጋጋሚ የሐይማኖታዊ ጥቃት ክስ ውድቅ አደረገች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 26.02.2026
ሰብስክራይብ

ናይጄሪያ በአሜሪካ የሚቀርብባትን ተደጋጋሚ የሐይማኖታዊ ጥቃት ክስ ውድቅ አደረገች

ናይጄሪያ ሐይማኖት ላይ ያነጣጠረ የመንግሥት ፖሊሲ "የላትም፣ ኖሯትም አያውቅም" ሲሉ የኢንፊርሜሽን ሚኒስትሩ መሐመድ ኢድሪስ በመግለጫቸው አስታውቀዋል። ሚኒስትሩ ክርስቲያኖች ኢላማ እየተደረጉ ነው በሚል በአሜሪካ በኩል በድጋሚ የቀረበውን ውንጀላ ውድቅ አድርገዋል።

"የጸጥታ ኃይሎቻችን እየተጋፈጡት ያለው ጥቃት በመንግሥት ፖሊሲ ወይም በሐይማኖታዊ አድልዎ አይመራም፡፡ ይልቁንም ሽብርተኝነት፣ የተደራጀ ወንጀልና ለረጅም ጊዜ የቆዩ የማኅበረሰብ ግጭቶችን ጨምሮ በተወሳሰቡ የደኅንነት ስጋቶች ምክንያት የሚከሰት ነው" ብለዋል።

የሀገሪቱ ሕገ-መንግሥት ለማንኛውም ዜጋ የማምለክ ነፃነትን እንደሚያረጋግጥም ሚኒስትሩ አጽንኦት ሰጥተዋል።

መግለጫው፤ ፕሬዚዳንት ትራምፕ በቅርቡ በናይጄሪያ "የክርስቲያኖች ጭፍጨፋ እየተፈጸመ ነው" በማለት ያቀረቡትን ክስ ደግፎ የወጣውን የአሜሪካ ኮንግረስ ሪፖርት ተከትሎ የመጣ ነው።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0