ኢትዮጵያ የአፍሪካውያን የሕክምና ቱሪዝም መዳረሻ እየሆነች ነው ተባለ
18:20 26.02.2026 (የተሻሻለ: 18:24 26.02.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ የአፍሪካውያን የሕክምና ቱሪዝም መዳረሻ እየሆነች ነው ተባለ
🩺 በጤናው ዘርፍ በተከናወኑ ተግባራት ቁጥራቸው እየጨመረ የመጣ አፍሪካውያን በዓይን፣ በጥርስ፣ በአንጎል፣ በመካንነት እና በሌሎች ስፔሻላይዝድ የሕክምና ዘርፎች አገልግሎት ለማግኘት ወደ ኢትዮጵያ እየመጡ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
ኢትዮጵያን ቀጣናዊ የሕክምና ቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ ከአዲስ አበባ በተጨማሪ በክልል ከተሞች ግዙፍ ሆስፒታሎች እየተገነቡና በዘመናዊ የሕክምና መሣሪያዎች እየተሟሉ መሆኑን የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጄ ዱጉማ ተናግረዋል፡፡
የሕክምና ባለሙያዎች በውጭ ሀገር በሰብ-ስፔሻሊቲ እንዲሠለጥኑ በማድረግ ረገድ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ መሆኑንም ሚኒስትር ዴታው ገልፀዋል።
መሠረታዊ የሕክምና መሣሪያዎችንና መድኃኒቶችን በሀገር ውስጥ የማምረት አቅም 40 በመቶ መድረሱንና በቀጣይ ዓመት ወደ 60 በመቶ ለማሳደግ መታቀዱን ሚኒስትር ዴኤታውን ጠቅሶ የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X