ናይጄሪያ የሀገር ውስጥ ምርትን ለማሳደግ ባልተቀነባበረ የሼአ ፍሬ ምርት ውጪ ንግድ ላይ የጣለችውን እገዳ ለአንድ ዓመት አራዘመች
17:54 26.02.2026 (የተሻሻለ: 18:04 26.02.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ናይጄሪያ የሀገር ውስጥ ምርትን ለማሳደግ ባልተቀነባበረ የሼአ ፍሬ ምርት ውጪ ንግድ ላይ የጣለችውን እገዳ ለአንድ ዓመት አራዘመች
የእገዳው መራዘም መንግሥት በሀገራዊ ምርቶች ላይ እሴት ለመጨመር እና ለኢንዱስትሪ ዕድገት የሚያደርገውን ጥረት የሚያጠናክር መሆኑን የፕሬዚዳንት ጽሕፈት ቤት መግለጫ አመልክቷል። የሼአ አምራች ማኅበረሰቦችን የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻል ያለመ መሆኑንም አክሏል።
ቁልፍ ጉዳዮች፦
የቆይታ ጊዜ፦ ማራዘሚያው እ.ኤ.አ ከየካቲት 26 ቀን 2026 እስከ የካቲት 25 ቀን 2027 ድረስ ይቆያል።
የኢኮኖሚ ግብ፦ ናይጄሪያ ከዓለም የሼአ ምርት 40 በመቶ ያህሉን ብትሸፍንም፤ ከ6.5 ቢሊዮን ዶላር የዓለም ገበያ ውስጥ 1 በመቶ ብቻ የሚሆነውን ነው የያዘችው። መንግሥት ዓመታዊ ገቢውን በአጭር ጊዜ ውስጥ 300 ሚሊዮን ዶላር፤ እስከ 2027 ደግሞ በአሥር እጥፍ ለማሳደግ አልሟል።
እገዳው እ.ኤ.አ በነሐሴ 2025 የተጣለውን የስድስት ወር ጊዜያዊ ዕርምጃ ተከትሎ የመጣ ነው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X