የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር 170 ሺህ ዜጎችን ከጎርፍ መፈናቀል ማዳኑን አስታወቀ
17:36 26.02.2026 (የተሻሻለ: 17:44 26.02.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር 170 ሺህ ዜጎችን ከጎርፍ መፈናቀል ማዳኑን አስታወቀ
ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ በአዋሽ፣ በሪፍት ቫሊ እና በኦሞ ጊቤ ተፋሰሶች ላይ ባከናወናቸው የጎርፍ መከላከል ሥራዎች 170 ሺህ ነዋሪዎችን ከመፈናቀል፣ 30 ሺህ ሄክታር የእርሻ መሬትን ደግሞ ከውድመት መታደጉን አስታውቋል።
ይህ የተሰማው ሚኒስቴሩ በዘርፉ ከተሠማራ (ኤስ. ደብሊው.ኤስ) አማካሪ ድርጅት ጋር በመሆን በኦሞ ጊቤ ተፋሰስ ላይ ያከናወነው የተግባራዊነት ጥናት ሪፖርት በሐዋሳ ከተማ ለባለድርሻ አካላት ባቀረበበት ወቅት ነው፡፡
የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ፤ ጥናቱ ቀደም ሲል የነበረውን የአስቸኳይ ጊዜ መከላከል ሥራ በዘላቂ ጥናትና ፕሮጀክቶች ለመተካት እየተከናወነ ያለው ተግባር አካል መሆኑን ገልፀዋል።
በጥናቱ የተገኙ ውጤቶችን መሠረት በማድረግ በሌሎች የሀገሪቱ ተፋሰሶች ላይም ተመሳሳይ የጎርፍ መከላከል ስትራቴጂዎችን ተግባራዊ ለማድረግ ታቅዷል መባሉን የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X