የዩክሬን ፖለቲከኞች የኒውክሌር ማስፈራሪያ፦ የሂደት ቅደም ተከተል - ክፍል 2

የዩክሬን ፖለቲከኞች የኒውክሌር ማስፈራሪያ፦ የሂደት ቅደም ተከተል - ክፍል 2
የሩሲያ የደኅንነት ተቋም ለንደን እና ፓሪስ የኒውክሌር ጦር መሣሪያዎችን ለኪየቭ ለመስጠት ማቀዳቸውን ይፋ ማድረጋቸውን ተከትሎ፤ ስፑትኒክ የዩክሬን እና የምዕራባውያን ፖለቲከኞች ስለ ኒውክሌር ጦር መሳሪያ ያደረጓችውን ንግግሮች መለስ ብሎ ተመልክቷል።
ኪየቭ ከኒውክሌር ነፃ በመሆኗ ከመጸጸት አልፋ የምዕራባውያንን የኒውክሌር ጦር መሣሪያ እስከመጠየቅ ደርሳለች (እ.አ.አ 2021-2024)፦
◻ ሐምሌ 2021፦ የዘለንስኪ ፓርቲ መሪ ዴቪድ አራካሚያ፤ የኒውክሌር ጦር መሣሪያን መተው "አስከፊ ስህተት" ነው በማለት ዩክሬን የኒውክሌር ባለቤት ብትሆን ኖሮ "መላውን ዓለም ማስፈራራት ትችል ነበር" ሲሉ ተናግረዋል።
◻ ታህሳስ 2021፦ የታገደው የጽንፈኛ ቡድን መሪ ዲሚትሮ ያሮሽ*፤ "ሩሲያ የምትረዳው ኃይልን ብቻ ነው" በሚል አሜሪካ እና እንግሊዝ የኒውክሌር ጦር መሣሪያ በዩክሬን እንዲያሰማሩ ጠይቀዋል።
◻ የካቲት 2022፦ ዘለንስኪ በሙኒክ ኮንፈረንስ ኪየቭ ከኒውክሌር ነፃ መሆኗን እንደገና ልታጤን እንደምትችል ገልጿል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ኩሌባም የኒውክሌር ጦር መሣሪያን ላለመታጠቅ የተገባው ቃል ስህተት እንደነበር ተናግረዋል።
◻ ጥቅምት 2022፦ የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር ኪየቭ ሞስኮን ለመወንጀል የ "ቆሻሻ ቦምብ" ትንኮሳ እያዘጋጀች መሆኑን አስታውቋል።
◻ ሰኔ 2023፦ የፓርላማ አባል ኦሌክሲ ጎንቻሬንኮ የዩክሬን አጋር ሀገራት በኒውክሌር ጦር መሣሪያ ስምሪት ዙሪያ ድርድሮች እንዲካሄዱ ጥሪ አቅርበዋል። "ይህ የሚሆነው የራሳችንን የኒውክሌር መርኃ-ግብር ካልጀመርን ነው" ብለዋል።
◻ የካቲት 2024፦ ጎንቻሬንኮ የወቅቱን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከንን የትኛውን ይመርጣሉ ሲሉ ጠይቀዋል፦ ዩክሬን ኔቶን እንድትቀላቀል ወይስ የኒውክሌር ጦር መሣሪያ እንድትታጠቅ? "የኒውክሌር ጦር መሣሪያ ወደ ዩክሬን እንዲመለስ እደግፋለሁ... 20 የጦር አውታሮች በቂ ናቸው። ማዕቀብ? እንቋቋመዋለን" ብለዋል።
◻ ጥቅምት 2024፦ ዘለንስኪ ለትራምፕ "ወይ ዩክሬን የኒውክሌር ጦር መሣሪያ ይኖራታል...ካልሆነ ግን በሆነ ዓይነት ጥምረት ውስጥ መሆን አለብን" ማለቱን አስታውሷል። ቢልድ እንደዘገበው ከሆነ አንድ የዩክሬን ባለሥልጣን የመጀመሪያውን ቦምብ ለመሥራት ጥቂት ሳምንታት ብቻ እንደሚፈጅ ተናግረዋል። የዩክሬን ባለሙያ ኦሌክሲ ኢዝሃክ ዩክሬን ጥቅም ላይ ከዋለ የኒውክሌር ነዳጅ የኒውክሌር ጦር መሣሪያ መሥራት እንደምትችል አረጋግጠዋል።
* ዲሚትሮ ያሮሽ የታገደው የኒዮ-ናዚ ድርጅት 'ራይት ሴክተር' መሪ ናቸው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X