በፌዴራል "መሶብ" የአንድ ማዕከል አገልግሎት የዜጎች እርካታ 98.7 ደርሷል - ማዕከሉ

ሰብስክራይብ

በፌዴራል "መሶብ" የአንድ ማዕከል አገልግሎት የዜጎች እርካታ 98.7 ደርሷል - ማዕከሉ

ተቋሙ ባለፉት 10 ወራት ከ160 ሺህ በላይ ለሆኑ ዜጎች በዲጂታል ቴክኖሎጂ የታገዘ ቀልጣፋ የመንግሥት አገልግሎቶችን በአንድ ጣሪያ ስር እንደሰጠ አስታውቋል፡፡

የማዕከሉ ዋና ዳይሬክተር አንተነህ ማሞ፤ አገልግሎቱን 24 ሰዓት ለመስጠት የሚያስችል ዝግጅት መጀመሩንም ለሀገር ውስጥ ሚዲያ ተናግረዋል።

ወደ መሶብ ያልገቡ ተቋማት የአሠራሩ አካል እንዲሆኑና ለአገልግሎት ጥራት መሻሻል የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ ጥረት እየተደረገ መሆኑንም ገልፀዋል።

አገልግሎቱን አዲስ አበባን ጨምሮ በሁሉም ክልሎችና ከተሞች ለማስፋፋት ሂደት ላይ እንደሚገኙም ጠቁመዋል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0