ዛምቢያ ከአሜሪካ ጋር ልትፈራረመ የነበረውን የ1 ቢሊዮን ዶላር+ የጤና ስምምነት "በአጠራጣሪ" ቅድመ ሁኔታዎች ምክንያት ለማዘግየት ወሰነች

© telegram sputnik_ethiopiaዛምቢያ ከአሜሪካ ጋር ልትፈራረመ የነበረውን የ1 ቢሊዮን ዶላር+ የጤና ስምምነት "በአጠራጣሪ" ቅድመ ሁኔታዎች ምክንያት ለማዘግየት ወሰነች
ዛምቢያ ከአሜሪካ ጋር ልትፈራረመ የነበረውን የ1 ቢሊዮን ዶላር+ የጤና ስምምነት በአጠራጣሪ ቅድመ ሁኔታዎች ምክንያት ለማዘግየት ወሰነች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 26.02.2026
ሰብስክራይብ

ዛምቢያ ከአሜሪካ ጋር ልትፈራረመ የነበረውን የ1 ቢሊዮን ዶላር+ የጤና ስምምነት "በአጠራጣሪ" ቅድመ ሁኔታዎች ምክንያት ለማዘግየት ወሰነች

በቀረበው የጤና ፈንድ ስምምነት "ከመንግሥት አቋምና ፍላጎት ጋር የማይጣጣም" ክፍል በመገኘቱ እንዲራዘም መደረጉን የሀገሪቱ ጤና ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ለምዕራባውያን መገናኛ ብዙኃን ተናግረዋል።

በመገናኛ ብዙኃን የተጠቀሰውና በተሠራጨው ረቂቅ ስምምነት ላይ የሰፈሩ ዋና ዋና ዝርዝሮች፦

◻ የአምስት ዓመቱ ስምምነት ኤች.አይ.ቪ፣ ወባ፣ የእናቶች ጤና እና የበሽታ ወረርሽኝ ዝግጁነትን ለመደገፍ የሚውል የአሜሪካ የገንዘብ ድጋፍን የሚሸፍን ሲሆን ከዛምቢያ ደግሞ 340 ሚሊዮን ዶላር ያህል የጋራ ፈንድ መዋጮ ይጠይቃል።

◻ በኅዳር ወር እንዲፈረም ታቅዶ የነበረ ቢሆንም በተሻሻለው ረቂቅ ላይ "አጠራጣሪ" አንቀጽ በመካተቱ መዘግየቱ ተዘግቧል።

◻ ቃል አቀባዩ ስለ ስምምነቱ ዝርዝር ይዘት ማብራሪያ ሳይሰጡ፤ ተጨማሪ ማሻሻያዎች እንዲደረጉ መጠየቁን ብቻ ገልጸዋል።

◻ ረቂቅ ስምምነቱ የጤና ፈንዱን ከማዕድን ዘርፍ ትብብር ጋር ከተያያዘ የተለየ "ሁለትዮሽ ስምምነት" ጋር እንደሚያቆራኘውና እስከ ሚያዝያ 1 ቀን ድረስ ስምምነት ካልተደረሰ ውሉ እንደሚቋረጥ ይገልጻል።

◻ አሜሪካ በመዳብ ምርት ከአፍሪካ ሁለተኛ ከሆነችው ዛምቢያ ጋር "ለማዕድን ዘርፍ ትብብር ምትክ ከፍተኛ የአሜሪካ ድጋፍ ጥቅል" ይፋ ለማድረግ ማቀዷን በታኅሣሥ ወር አስታውቃ ነበር።

በተመሳሳይ በቅርቡ ዚምባብዌ "እኩል ያልሆኑ ውሎችን" በመጥቀስ ከ367 ሚሊዮን ዶላር የጤና ስምምነት መውጣቷ የሚታወስ ሲሆን የኬንያ የ1.6 ቢሊዮን ዶላር ስምምነትም በሕግ ክርክር ምክንያት እንደታገደ ይገኛል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0