ተገንጣይዋ የሶማሊያ ክልል ሶማሊላንድ፤ በተናጠል በእስራኤል አምባሳደር እንደሾመች ይፋ አደረገች
15:03 26.02.2026 (የተሻሻለ: 15:44 26.02.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ተገንጣይዋ የሶማሊያ ክልል ሶማሊላንድ፤ በተናጠል በእስራኤል አምባሳደር እንደሾመች ይፋ አደረገች
የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሹመቱን በመቀበል በቅርቡ ወደ ሀርጌሳ አምባሳደር እንደሚልክ አስታውቋል።
አውድ፦
ሶማሊያ፤ እስራኤል ለሶማሊላንድ የሰጠችውን እውቅና በዓለም አቀፍ ሕግ መሠረት "ሕገ-ወጥ" ነው በማለት በተደጋጋሚ ያወገዘች ሲሆን በግዛቷ ላይ የሚደረግ ማንኛውንም የውጭ ጣልቃ ገብነት እንደምትከላከል ዝታለች።
እስራኤል እ.ኤ.አ በታኅሣሥ 2025 ለሶማሊላንድ እውቅና ሰጥታለች፡፡ ይህም በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ያልተሰጣትንና በ1990ዎቹ አጋማሽ ከሶማሊያ መገንጠሏን ላወጀችው ሶማሊላንድ በይፋ እውቅና የሰጠች የመጀመሪያዋ ሀገር አድርጓታል።
ተንቀሳቃሽ ምሥሉ የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ሳር በጥር ወር ወደ ሀርጌሳ ያደረጉትን ጉብኝት ያሳያል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X