ኢትዮጵያ የሰው ሠራሽ አስተውህሎት ትምህርትን ከአንደኛ ደረጃ ጀምሮ ልትሰጥ ነው

© telegram sputnik_ethiopiaኢትዮጵያ የሰው ሠራሽ አስተውህሎት ትምህርትን ከአንደኛ ደረጃ ጀምሮ ልትሰጥ ነው
ኢትዮጵያ የሰው ሠራሽ አስተውህሎት ትምህርትን ከአንደኛ ደረጃ ጀምሮ ልትሰጥ ነው - Sputnik አፍሪካ, 1920, 26.02.2026
ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ የሰው ሠራሽ አስተውህሎት ትምህርትን ከአንደኛ ደረጃ ጀምሮ ልትሰጥ ነው

የትምህርት ሚኒስቴር የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂን ለማሳካት የሰው ሠራሽ አስተውሎት እና የዲጂታል ክህሎት ትምህርትን ከአንደኛ እስከ 12ኛ ክፍል ባለው የትምህርት ሥርዓት ውስጥ ለማካተት ዝግጅት እያደረገ መሆኑን አስታውቋል።

ይህ ጅምር ከዲጂታሉ ዓለም ጋር እኩል የሚራመዱ፣ ብቁና ተወዳዳሪ ታዳጊዎችንና ወጣቶችን ለማፍራት ብሎም ሀገሪቱን በዲጂታል ዘርፍ ተመራጭ ለማድረግ ትልቅ መሠረት እንደሚጥል ታምኖበታል ተብሏል።

‍ በተያያዘም በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚገኙ መምህራንና ተማሪዎች የዲጂታል ክህሎታቸውን እንዲያሳድጉ በአምስት ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ኮደርስ ሥልጠና ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘገባ አመላክቷል።

በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለጸገ ምሥል

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0