የሩሲያ የፓስፊክ ጦር መርከቦች ቡድን በሕንድ በተካሄደው የሚላን 2026 ልምምድ ላይ የባሕር ኃይል ብቃቱን አሳየ

ሰብስክራይብ

የሕንድ ባሕር ኃይል የሚያካሂደው 'ሚላን 2026' የባሕር ልምምድ በቪሳካፓትናም የባሕር ዳርቻ፤ በሕንድ የጥቃት አውሮፕላን ተሸካሚ መርከብ 'አይ.ኤን.ኤስ ቪክራንት' ላይ በተካሄደ የመዝጊያ ሥነ-ሥርዓት ተጠናቋል።

"ወዳጅነት፣ ትብብር እና አጋርነት" በሚል መሪ ቃል በተካሄደው በዚህ ልምምድ ላይ ከተሳተፉ 42 መርከቦች እና ሰርጓጅ መርከቦች መካከል፤ የሩሲያ ባሕር ኃይል በፓስፊክ የጦር መርከቦች ቡድን ፍሪጌት 'ማርሻል ሻፖሽኒኮቭ' መወከሉን የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል።

በቤንጋል ባሕረ ሰላጤ ውስጥ ለአምስት ቀናት በቆየው በዚህ መርኃ-ግብር፤ የሩሲያ መርከበኞች ከሌሎች ተሳታፊ ሀገራት የባሕር ኃይሎች ጋር በመሆን የተቀናጀ እንቅስቃሴ፣ በባሕርና በአየር ኢላማዎች ላይ የቀጥታ ተኩስ ልምምዶችን እንዲሁም የሰርጓጅ መርከብ መከላከያ ስልቶችን አከናውነዋል።

ተሳታፊ መርከቦች የፈንጂ ስጋት ባለባቸው ውኃዎች ውስጥ የማለፍ፣ በጠላት የተያዘን መርከብ የማስለቀቅ እና የሲቪል መርከቦችን ደህንነት ለመጠበቅ የሚያስችሉ የፍተሻ ሥራዎችን በተግባር ተለማምደዋል።

የ 'ሚላን' ልምምድ እ.ኤ.አ ከ1995 ጀምሮ በየሁለት ዓመቱ በሕንድ አስተናጋጅነት ሲካሄድ ቆይቷል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
የሩሲያ የፓስፊክ ጦር መርከቦች ቡድን በሕንድ በተካሄደው የሚላን 2026 ልምምድ ላይ የባሕር ኃይል ብቃቱን አሳየ - Sputnik አፍሪካ
1/4

2/4

3/4

4/4
1/4
2/4
3/4
4/4
አዳዲስ ዜናዎች
0