ለሩሲያ እና ኢትዮጵያ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት 128ኛ ዓመት እንኳን አደረሳችሁ - በኢትዮጵያ የሩሲያ ኤምባሲ

ሰብስክራይብ

ለሩሲያ እና ኢትዮጵያ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት 128ኛ ዓመት እንኳን አደረሳችሁ - በኢትዮጵያ የሩሲያ ኤምባሲ

የሁለቱ ሀገራት ታሪካዊ ግንኙነት አንድ ክፍለ ዘመን መሻገሩንና አሁን ላይ በንግድ፣ በኒውክሌር ቴክኖሎጂ እና በፖለቲካ ዘርፎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተጠናከረ እንደሚገኝ ኤምባሲው አስታውቋል።

ኤምባሲው በመልካም ምኞት መግለጫው ያነሳቸው የትብብር ውጤቶች፦

የንግድ ዕድገት፦ የሁለቱ ሀገራት የንግድ ልውውጥ በ3 እጥፍ አድጎ $435 ሚሊዮን ዶላር ደርሷል።

የኒውክሌር ትብብር፦ በሮሳቶም እና በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል መካከል የተፈረመው ስምምነት ወደ ተግባር ተሸጋግሯል።

ሩሲያ ማዳበሪያ፣ የግብርና ማሽነሪ እና የኢነርጂ መሣሪያዎችን ለኢትዮጵያ ስታቀርብ፤ ኢትዮጵያ በበኩሏ ቡና፣ አበባ እና ጨርቃጨርቅን ወደ ሩሲያ በመላክ ላይ እንደምትገኝ ተጠቁሟል።

ሁለቱ ሀገራት በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እና በሌሎች ዓለም አቀፍ መድረኮች ያላቸውን ቅንጅት ለማጠናከር ቃል መግባታቸውን ኤምባሲው ጠቅሷል።

በመስከረም ወር (ምሥል) ፕሬዚዳንት ፑቲን እና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሞስኮ ተገናኝተው የሁለትዮሽ ውይይት ማድረጋቸው የሚታወስ ነው።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0