የኢኮዋስ ወታደራዊ አዛዦች የተጠባባቂ ኃይል ስምሪትን በተመለከት በሴራሊዮን እየመከሩ ነው

ሰብስክራይብ

የኢኮዋስ ወታደራዊ አዛዦች የተጠባባቂ ኃይል ስምሪትን በተመለከት በሴራሊዮን እየመከሩ ነው

🪖 የኢኮዋስ አባል ሀገራት የጦር አዛዦች ስብሰባ ማክሰኞ በፍሪታውን የተጀመረ ሲሆን ለሦስት ቀናት እንደሚቆይ ተገልጿል።

በስብሰባው እያንዳንዱ ሀገር ለዚህ ግብረ ኃይል የሚያዋጣውን የወታደር ቁጥር ይፋ ያደርጋል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን በመጀመሪያው ዙር ወደ ሁለት ሺህ የሚጠጉ ወታደሮች ይሰማራሉ ተብሎ እንደሚገመት የአካባቢው መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

የኢኮዋስ ተጠባባቂ ኃይል ምንድን ነው?

እ.ኤ.አ በመጋቢት 2025 በናይጄሪያ አቡጃ የተሰበሰቡት የኢኮዋስ ጦር አዛዦች፤ ሽብርተኝነትን እና ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን ለመዋጋት እንዲሁም በምዕራብ አፍሪካ ቀጣና መረጋጋትን ለማረጋገጥ "ተጠባባቂ ኃይል" ወደ ሥራ እንዲገባ ወስነዋል። ግብረ ኃይሉ ከአባል ሀገራት የተውጣጡ የወታደራዊ፣ ፖሊስ እና ሲቪል ባለሙያዎችን ያቀፈ ነው።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0