አፍሪካ በተጋነነ የብድር ስጋት ግምት በቢሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር እያጣች ነው - የዛምቢያ ባለሥልጣን

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱአፍሪካ በተጋነነ የብድር ስጋት ግምት በቢሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር እያጣች ነው - የዛምቢያ ባለሥልጣን
አፍሪካ በተጋነነ የብድር ስጋት ግምት በቢሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር እያጣች ነው - የዛምቢያ ባለሥልጣን - Sputnik አፍሪካ, 1920, 25.02.2026
ሰብስክራይብ

አፍሪካ በተጋነነ የብድር ስጋት ግምት በቢሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር እያጣች ነው - የዛምቢያ ባለሥልጣን

የአፍሪካ ሀገራት በሌሎች ክልሎች ካሉ አቻዎቻቸው ጋር ሲነጻጸር ሦስት በመቶ የሚልቅ የብድር ወለድ እንዲከፍሉ እየተገደዱ መሆኑን የዛምቢያ የገንዘብ ሚኒስቴር ጸሐፊ ፌሊክስ ንኩሉኩሳ ገልጸዋል። አክለውም ይህ "የአድልዎ ክፍያ" አህጉሪቱ በየዓመቱ ብድር ለመሸፈን እስከ 75 ቢሊዮን ዶላር የሚደርስ ተጨማሪ ወጪ እንድታወጣ እንዳደረጋት አስረድተዋል፡፡

በ2026ቱ የአፍሪካ ገበያዎች ኮንፈረንስ ላይ ንግግር ያደረጉት ንኩሉኩሳ፤ በባለሀብቶች ዘንድ "አፍሪካ የፖለቲካ አለመረጋጋትና የመጥፎ አስተዳደር መገለጫ ብቻ ናት" የሚለውን የተሳሳተ አመለካከት ተቃውመዋል።

እሳቸው የጠቀሱት መረጃ እንደሚያሳየው የአፍሪካ የብድር ክፍያ ማቋረጥ ምጣኔ 5.5 በመቶ ሲሆን ይህም ከእስያ (11.9 በመቶ) በግማሽ የሚቀንስ እንዲሁም ከላቲን አሜሪካ (14.5 በመቶ) ጋር ሲነጻጸር በሲሶ ያነሰ ነው። ይሁን እንጂ የአኅጉሪቱ የብድር ወጪ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ሆኖ ቀጥሏል።

ንኩሉኩሳ የችግሩ ከፊል ምንጭ በብድር አያያዝ ረገድ ካለው ግልጽነት እጥረት እንደሚመነጭ በመጥቀስ፤ የአፍሪካ ሀገራት ተጠያቂነትን እንዲያሰፍኑ አሳስበዋል።

እ.ኤ.አ በ2020 የብድር ክፍያዋን ያቋረጠችው ዛምቢያ፤ ከዚያ ወዲህ የበጀት ጉድለትን ከጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት በ3 በመቶ በታች ማቆየት፣ ዓመታዊ የብድር እቅዶችን ለፓርላማ ማቅረብ እና የየሩብ ዓመቱን የብድር መመዝገቢያ ይፋ ማድረግን ጨምሮ የተለያዩ ማሻሻያዎችን አስተዋውቃለች።

በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለጸገ ምሥል

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0