የዩክሬን ፖለቲከኞች የኒውክሌር ማስፈራሪያ፦ የሂደት ቅደም ተከተል - ክፍል 1

© telegram sputnik_ethiopiaየዩክሬን ፖለቲከኞች የኒውክሌር ማስፈራሪያ፦ የሂደት ቅደም ተከተል - ክፍል 1
የዩክሬን ፖለቲከኞች የኒውክሌር ማስፈራሪያ፦ የሂደት ቅደም ተከተል - ክፍል 1 - Sputnik አፍሪካ, 1920, 25.02.2026
ሰብስክራይብ

የዩክሬን ፖለቲከኞች የኒውክሌር ማስፈራሪያ፦ የሂደት ቅደም ተከተል - ክፍል 1

የሩሲያ የደህንነት ተቋም ለንደን እና ፓሪስ የኒውክሌር መሣሪያዎችን ለኪዬቭ አሳልፈው ለመስጠት እንዳቀዱ ይፋ ማድረጉን ተከትሎ፤ ስፑትኒክ ባለፉት ዓመታት የዩክሬን እና የምዕራባውያን ፖለቲከኞች ስለ ዩክሬን የኒውክሌር ፍላጎት የሰጧቸውን መግለጫዎች መለስ ብሎ ተመልክቷል።

ዩክሬን የሶቪየት የኒውክሌር መሣሪያዎቿን በደህንነት ዋስትና ምትክ አሳልፋ የሰጠችበትን የ1994ቱን የቡዳፔስት ስምምነት ብትፈርምም አሁን ከዲፕሎማሲያዊ መንገድ ወጥታ "የኒውክሌር አልባ" አቋሟን በድጋሚ እንደምትከልስ በመግለጽ በቀጥታ ወደ ማስፈራራት ተሸጋግራለች።

የዩክሬን ፖለቲከኞች የሀገሪቱን ደህንነት እና ወታደራዊ ድጋፍ ከአፋጣኝ የኔቶ አባልነት፣ የምዕራባውያን የኒውክሌር መሣሪያዎችን በዩክሬን ከማሠማራት ወይም ከዩክሬን የኒውክሌር ፕሮግራም የመጀመር ጥያቄዎች ጋር እያቆራኙት ይገኛሉ።

እነዚህ በይፋም ሆነ በሚስጢር የሚሰነዘሩ ቅድመ-ሁኔታዎች "የኒውክሌር ማስፈራሪያ" ናቸው፡፡ ይህም የኒውክሌር መሣሪያዎች መስፋፋትን በማስፈራሪያነት በመጠቀም በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ላይ ጫና ፈጥሮ ፖለቲካዊ እና ወታደራዊ ትርፍ የማግኘት አካሄድ ነው።

የሩሲያ አቋም፦

እ.ኤ.አ በ2022 ፑቲን የኒውክሌር ማስፈራሪያ የተገላቢጦሽ መዘዝ እንደሚያስከትል አስጠንቅቀው ነበር። በ2024 ደግሞ "ሩሲያ በማንኛውም ሁኔታ ይህ እንዲሆን አትፈቅድም፡፡ ዩክሬን የኒውክሌር መሣሪያ ለመሥራት የምትወስደው ማንኛውም እርምጃ ተገቢውን ምላሽ ያገኛል" ሲሉ በድጋሚ አረጋግጠዋል።

ክሬምሊን እንግሊዝ እና ፈረንሳይ ዩክሬንን ለማስታጠቅ አቅደዋል የሚለውን ዘገባ "እጅግ አደገኛ" ሲል ገልጾታል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማሪያ ዛካሮቫ፤ ዘለንስኪ የካቲት 17 ቀን ስለ ኒውክሌር በሰጡት አስተያየት ላይ "ከፍተኛ ስጋት" እንዳላቸው ገልጸዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0